2 ዜና መዋዕል 22:8 - Compare All Versions
2 ዜና መዋዕል 22:8 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ኢዩም የአክዓብን ቤት ይበቀል ዘንድ የይሁዳን መሳፍንትና አካዝያስን ያገለግሉ የነበሩትን የአካዝያስን ወንድሞች አግኝቶ ገደላቸው።
2 ዜና መዋዕል 22:8 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ኢዩ በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድ በሚፈጽምበት ጊዜ፣ አካዝያስን ያጅቡ የነበሩትን የይሁዳን መሳፍንትና የዘመዶቹን ወንዶች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።
2 ዜና መዋዕል 22:8 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድን ሲፈጽም የይሁዳን መሳፍንትና አካዝያስን ያገለግሉ የነበሩትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።
2 ዜና መዋዕል 22:8 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ኢዩ በአክዓብ ሥርወ መንግሥት ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመፈጸም ላይ በነበረበት ጊዜ አካዝያስን አጅበው ከእርሱ ጋር መጥተው የነበሩትን የይሁዳ መሪዎችና የአካዝያስን ዘመዶች በዚያ አግኝቶ ሁሉንም ገደላቸው።
2 ዜና መዋዕል 22:8 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ኢዩም በአክዓብ ቤት ላይ ፍርድን ሲፈጽም የይሁዳን መሳፍንትና አካዝያስን ያገለግሉ የነበሩትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አግኝቶ ገደላቸው።