2 ዜና መዋዕል 14:5 - Compare All Versions

2 ዜና መዋዕል 14:5 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከእያንዳንዱም የይሁዳ ከተሞች የማምለኪያ ኰረብቶችንና የዕጣን መሠዊያዎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በርሱ አገዛዝ ዘመን ሰላም አገኘች።

2 ዜና መዋዕል 14:5 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የኰረብታ መስገጃዎች ስፍራዎችንና ዕጣን የሚታጠንባቸውን መሠዊያዎች ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ስላስወገደ፥ በእርሱ ዘመነ መንግሥት ሰላም ሰፈነ፤

2 ዜና መዋዕል 14:5 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ የጣ​ዖት መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ች​ንና ምስ​ሎ​ችን አስ​ወ​ገደ፤ መን​ግ​ሥ​ቱም በእ​ርሱ ሥር በሰ​ላም ተቀ​መ​ጠች።

2 ዜና መዋዕል 14:5 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችና የፀሐይ ምስሎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች።

2 ዜና መዋዕል 14:5 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ የኮረብታውን መስገጃዎችና የዕጣን መሠዊያዎቹን አስወገደ፤ መንግሥቲቱም በእርሱ ሥር ሰላም የሰፈነባት ሆነች።