1 ተሰሎንቄ 4:9-12
1 ተሰሎንቄ 4:9-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እናንተ ራሳችሁ እርስ በርሳችሁ ልትዋደዱ በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፥ ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ይጽፍላችሁ ዘንድ አያስፈልጋችሁም፤ እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገ ግን ወንድሞች ሆይ!ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቅቁ፥ እንዳዘዝናችሁም በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።
1 ተሰሎንቄ 4:9-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም እንዲጽፍላችሁ አያስፈልግም፤ ምክንያቱም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ እናንተ ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና። በመላዪቱ መቄዶንያ የሚገኙትን ወንድሞች ሁሉ እንደምትወድዷቸው የታወቀ ነው፤ ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፤ ከዚህ በበለጠ እንድታደርጉት እንመክራችኋለን። ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁ በገዛ እጃችሁ ሥሩ፤ በጸጥታ ኑሩ፤ በራሳችሁ ጕዳይ ላይ ብቻ አተኵሩ። ይኸውም፣ በዕለት ተለት ኑሯችሁ በውጭ ባሉት ዘንድ እንዲያስከብራችሁና በማንም ሰው ላይ ሸክም እንዳትሆኑ ነው።
1 ተሰሎንቄ 4:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እናንተ ራሳችሁ እርስ በርሳችሁ ልትዋደዱ በእግዚአብሔር ተምራችኋልና ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ይጽፍላችሁ ዘንድ አያስፈልጋችሁም፤ እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።
1 ተሰሎንቄ 4:9-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርስ በርስ ስለ መዋደድ እናንተ ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ስለ ተማራችሁ ስለዚህ ጉዳይ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልግም። በመላ መቄዶንያ ያሉትንም ወንድሞች ሁሉ ትወዳላችሁ፤ ሆኖም ወንድሞች ሆይ፥ አሁን የምንመክራችሁ ይበልጥ እንድትወዱ ነው፤ በጸጥታም ለመኖር እንድትጣጣሩ እና የራሳችሁን ጉዳይ እንድታስቡ ከዚህ በፊት እንዳዘዝናችሁም በገዛ እጃችሁ እንድትሠሩ ነው። በዚህ ዐይነት በማያምኑት ሰዎች ዘንድ የተከበራችሁ ትሆናላችሁ፤ የማንም ጥገኛ አትሆኑም።
1 ተሰሎንቄ 4:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እናንተ ራሳችሁ የእርስ በእርስ መዋደድን በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፥ ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ በእርግጥ በመላ መቄዶንያ ላሉት ወንድሞች ሁሉ እንዲሁ አድርጋችኋል። ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! እነዚህን አብዝታችሁ እንድታደርጉ በጸጥታ ለመኖር እንድትተጉ፥ በራሳችሁም ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩ፥ እንዳዘዝናችሁም በራሳችሁ እጅ እንድትሰሩ እንለምናችኋለን፤ በዚህም በማንም ላይ ሸክም እንዳትሆኑና በውጭ ባሉት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱ ነው።