1 ሳሙኤል 8:8
1 ሳሙኤል 8:8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤
1 ሳሙኤል 8:8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከግብፅ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክትን በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል።
1 ሳሙኤል 8:8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ዕለት አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው።
1 ሳሙኤል 8:8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከግብጽ ካወጣኋቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እንግዶች አማልክት በማምለካቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እንዲሁ በአንተ ደግሞ ያደርጉብሃል።