1 ሳሙኤል 8:19-20
1 ሳሙኤል 8:19-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን፤ እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፤ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላታችንን ይዋጋል” አሉት።
1 ሳሙኤል 8:19-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እንቢ በማለት፤ እንዲህ አሉ፤ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን፤ እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፣ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።”
1 ሳሙኤል 8:19-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሕዝቡ ግን የሳሙኤልን ነገር ይሰማ ዘንድ እንቢ አለ፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን ንጉሥ ይሁንልን፥ እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፥ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፥ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት።