1 ሳሙኤል 5:11 - Compare All Versions

1 ሳሙኤል 5:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ልከ​ውም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች ሁሉ ሰብ​ስ​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ታቦት ስደ​ዱ​አት፤ እኛ​ንና ሕዝ​ባ​ች​ንን እን​ዳ​ት​ገ​ድል በስ​ፍ​ራዋ ትቀ​መጥ” አሉ።

1 ሳሙኤል 5:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዦች በሙሉ ጠርተው፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ አለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።

1 ሳሙኤል 5:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና፥ የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ፥ እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ።

1 ሳሙኤል 5:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እንደገና ወደ ፍልስጥኤማውያን ነገሥታት ሁሉ መልእክተኞች ልከው “እኛንና ቤተሰባችንን ሁሉ ከመፍጀቱ በፊት የእስራኤልን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ስፍራው መልሳችሁ ላኩ” አሉ፤ እግዚአብሔር በብርቱ ስለ ቀጣቸው በመላ ከተማይቱ የሚያስጨንቅ የሞት ፍርሀት ነበር፤

1 ሳሙኤል 5:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።