1 ሳሙኤል 21:12-13
1 ሳሙኤል 21:12-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዳዊትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፤ የጌትንም ንጉሥ አንኩስን እጅግ ፈራ። በፊቱም መልኩን ለወጠ፤ በዚያችም ቀን አመለጠ። በከተማውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፤ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።
1 ሳሙኤል 21:12-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጋትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው። ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደ ሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፣ ልጋጉንም በጢሙ ላይ እያዝረበረበ እንደ እብድ ሆነ።
1 ሳሙኤል 21:12-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዳዊትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፥ የጌትንም ንጉሥ አንኩስን እጅግ ፈራ። በፊታቸውም አእምሮውን ለወጠ፥ በያዙትም ጊዜ እንደ እብድ ሆነ፥ በበሩም መድረክ ላይ ተንፈራፈረ፥ ልጋጉም በጢሙ ላይ ይወርድ ነበር።