1 ሳሙኤል 20:32-33 - Compare All Versions
1 ሳሙኤል 20:32-33 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፥ “ስለ ምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ብሎ መለሰለት። ሳኦልም ሊገድለው በዮናታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ይገድለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈረጠች ዐወቀ።
1 ሳሙኤል 20:32-33 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
ዮናታንም፣ “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” ሲል አባቱን ጠየቀ። ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፣ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቈርጦ መነሣቱን ዐወቀ።
1 ሳሙኤል 20:32-33 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፦ ስለ ምን ይሞታል? ያደረገውስ ምንድር ነው? ብሎ መለሰለት። ሳኦልም ሊወጋው ጦሩን ወረወረበት፥ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ፈጽሞ ሊገድለው እንደ ፈቀደ አወቀ።
1 ሳሙኤል 20:32-33 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። ከዚህም የተነሣ ዮናታንን ለመግደል የያዘውን ጦር ወረወረበት፤ ስለዚህም ዮናታን አባቱ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቊርጥ ውሳኔ ማድረጉን አረጋገጠ፤
1 ሳሙኤል 20:32-33 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፥ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሣቱን ዐወቀ።