1 ሳሙኤል 20:18-42

1 ሳሙኤል 20:18-42 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዮና​ታ​ንም አለው፥ “ነገ መባቻ ነው፤ መቀ​መ​ጫ​ህም ባዶ ሆኖ ይገ​ኛ​ልና ትታ​ሰ​ባ​ለህ። ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ለ​ገህ ጊዜ ትመ​ጣና ነገሩ በተ​ደ​ረ​ገ​በት ቀን በተ​ሸ​ሸ​ግ​ህ​በት ስፍራ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ በኤ​ር​ገብ ድን​ጋ​ይም አጠ​ገብ ቈይ። እኔም በዓ​ላማ ላይ እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ ብዬ ሦስት ፍላ​ጻ​ዎ​ችን ወደ ዓላ​ማው እወ​ረ​ው​ራ​ለሁ። እነ​ሆም፦ ሂድ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ፈልግ ብዬ ብላ​ቴ​ና​ውን እል​ካ​ለሁ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወደ​ዚህ ነው፤ ይዘ​ኸው ወደ እኔ ና ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ለአ​ንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለ​ብ​ህም። ብላ​ቴ​ና​ውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ና​ብ​ቶ​ሃ​ልና መን​ገ​ድ​ህን ሂድ። አን​ተና እኔም ስለ ተነ​ጋ​ገ​ር​ነው፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ምስ​ክር ነው።” ዳዊ​ትም በሜ​ዳው ተሸ​ሸገ፤ መባ​ቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመ​ብ​ላት ተቀ​መጠ። ንጉ​ሡም እንደ ቀድ​ሞው በግ​ንቡ አጠ​ገብ በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ቆመ፤ አቤ​ኔ​ርም በሳ​ኦል አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ የዳ​ዊ​ትም ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ። ሳኦ​ልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆ​ናል፤ ምን​አ​ል​ባ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም ይሆ​ናል፤ በእ​ው​ነ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም” ብሎ አስ​ቦ​አ​ልና በዚያ ቀን ምንም አል​ተ​ና​ገ​ረም። ከመ​ባ​ቻም በኋላ በማ​ግ​ሥቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን የዳ​ዊት ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ፤ ሳኦ​ልም ልጁን ዮና​ታ​ንን፥ “የእ​ሴይ ልጅ ትና​ትና ዛሬ ወደ ግብር ያል​መጣ ስለ​ምን ነው?” አለው። ዮና​ታ​ንም ለሳ​ኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተ​ማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግ​ሮኝ ተሰ​ና​ብ​ቶ​ኛል። እር​ሱም፥ “ዘመ​ዶቼ በከ​ተማ ውስጥ መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና፥ ወን​ድ​ሞቼም ጠር​ተ​ው​ኛ​ልና እባ​ክህ! አሰ​ና​ብ​ተኝ፤ አሁ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆነ ልሂ​ድና ወን​ድ​ሞ​ቼን ልይ አለ፤ ስለ​ዚህ ወደ ንጉሥ ማዕድ አል​መ​ጣም” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ሳኦ​ልም በዮ​ና​ታን ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “አንተ የከ​ዳ​ተ​ኞች ሴቶች ልጅ! የእ​ሴ​ይን ልጅ ለአ​ንተ ማፈ​ርያ፥ ለእ​ና​ት​ህም ኀፍ​ረተ ሥጋ ማፈ​ርያ እንደ መረ​ጥህ እኔ አላ​ው​ቅ​ምን? የእ​ሴይ ልጅ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ መን​ግ​ሥ​ትህ አት​ጸ​ናም፤ አሁ​ንም ሞት የሚ​ገ​ባው ነውና ያን ብላ​ቴና ያመ​ጡት ዘንድ ላክ” አለው። ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል፥ “ስለ ምን ይሞ​ታል? ምንስ አደ​ረገ?” ብሎ መለ​ሰ​ለት። ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ። አባቱ በእ​ርሱ ላይ ክፉ ነገ​ርን ሊያ​ደ​ርግ ስለ ቈረጠ ዮና​ታን ስለ ዳዊት አዝ​ኖ​አ​ልና እጅግ ተቈ​ጥቶ ከማ​ዕዱ ተነሣ፤ በመ​ባ​ቻ​ውም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ግብር አል​በ​ላም። እን​ዲ​ህም ሆነ በነ​ጋው ዮና​ታን ከዳ​ዊት ጋር ምል​ክት ለማ​ድ​ረግ ወደ ተቃ​ጠ​ረ​በት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ታናሽ ብላ​ቴና ነበረ። ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ሮጠህ የም​ወ​ረ​ው​ራ​ቸ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች ፈል​ግ​ልኝ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም በሮጠ ጊዜ ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ማዶ አሳ​ልፎ ወረ​ወ​ረው። ብላ​ቴ​ና​ውም ዮና​ታን ፍላ​ጻ​ውን ወደ ወረ​ወ​ረ​በት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮና​ታን፥ “ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወዲያ ነው” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ። ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ። ዮና​ታ​ንና ዳዊት ብቻ ነገ​ሩን ያውቁ ነበር እንጂ ብላ​ቴ​ናው ምንም አያ​ው​ቅም ነበር። ዮና​ታ​ንም መሣ​ሪ​ያ​ውን ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጥቶ፥ “ሂድ ወደ ከተማ ግባ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ። ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።

1 ሳሙኤል 20:18-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ነገ የወር መባቻ በዓል ነው፤ መቀመጫህ ባዶ ስለሚሆን፣ አለመኖርህ ይታወቃል። ከነገ ወዲያ ምሽት ላይ ይህ ችግር በተፈጠረ ዕለት ወደ ተደበቅህበት ስፍራ ሂድና ኤዜል በተባለው ድንጋይ አጠገብ ቈይ። እኔም በአንድ ዒላማ ላይ እንደሚያነጣጥር ሰው ወደ ድንጋዩ አጠገብ ሦስት ፍላጻ እወረውራለሁ፤ ከዚያም፣ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፣ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደ ሆነ፣ ሕያው እግዚአብሔርን! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ አደጋም የለም፤ ውጣና ና። ነገር ግን ልጁን፣ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንድትሄድ ፈቅዷልና ሂድ። አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ እግዚአብሔር በመካከላችን ለዘላለም ምስክር ነው።” ስለዚህም ዳዊት በዱር ተደበቀ፤ የወር መባቻ በዓል በተከበረበት ጊዜ፣ ንጉሡ ግብር ለመብላት ተቀመጠ፤ ንጉሡ እንደ ወትሮው በግድግዳው አጠገብ ተቀመጠ፤ ዮናታን ከፊት ለፊቱ፣ አበኔር ደግሞ ከአጠገቡ ተቀመጡ፤ የዳዊት መቀመጫ ግን ባዶ ነበር። ሳኦልም፣ “ዳዊት በሥርዐቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፣ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። በማግስቱም፣ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፣ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፣ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ዮናታንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም እንዲሄድ እፈቅድለት ዘንድ አጥብቆ ለመነኝ። እርሱም ‘ቤተ ሰባችን በከተማዪቱ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያደርግ በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛልና ልሂድ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ወንድሞቼን ለማየት እንድሄድ አሰናብተኝ’ አለኝ። በንጉሡ ግብር ላይ ሳይገኝ የቀረውም በዚህ ምክንያት ነው።” ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አንተ የዚያች ጠማማና ዐመፀኛ ሴት ልጅ! ለአንተው ለራስህ ውርደት፣ ለወላጅ እናትህም ዕፍረት ከሚሆነው ከእሴይ ልጅ ጋራ መግጠምህን የማላውቅ መሰለህ? የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንህ መንግሥትህ አትጸኑም። መሞት ስለሚገባው፣ ሰው ላክና አስመጣልኝ!” ዮናታንም፣ “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” ሲል አባቱን ጠየቀ። ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፣ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቈርጦ መነሣቱን ዐወቀ። ዮናታንም በታላቅ ቍጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። በማግስቱም ጧት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፣ ከዳዊት ጋራ ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ ልጁንም፣ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፣ ከርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፣ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው። እርሱም “ቶሎ በል! ፍጠን! አትቁም!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው ተመለሰ። ከዮናታንና ከዳዊት በቀር ልጁ ስለዚህ ነገር የሚያውቀው አንዳች አልነበረም። ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያውን ለልጁ ሰጥቶ፣ “ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። ልጁ ከሄደ በኋላ፣ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፣ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል እግዚአብሔር ለዘላለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በእግዚአብሔር ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

1 ሳሙኤል 20:18-42 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዮናታንም አለው፦ ነገ መባቻ ነው፥ መቀመጫህም ባዶ ሆኖ ይገኛልና ትታሰባለህ። ሦስት ቀንም ያህል ቆይ፥ ከዚህም በኋላ ፈጥነህ ውረድ፥ ነገሩም በተደረገበት ቀን ወደ ተሸሸግህበት ስፍራ ሂድ፥ በኤዜል ድንጋይም አጠገብ ቆይ። እኔም በዓላማ ላይ እወረውራለሁ ብዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደ አጠገቡ እወረውራለሁ። እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎችን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልከዋለሁ፥ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፥ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት ነውና ምንም የለብህም። ብላቴናውን ግን፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ያልሁት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። አንተና እኔም ስለ ተነጋገርነው፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለዘላለም በመካከላችን ምስክር ነው። ዳዊትም በሜዳው ተሸሸገ፥ መባቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመብላት ተቀመጠ። ንጉሡም እንደ ቀድሞው በግንቡ አጠገብ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፥ ዮናታንም ቆሞ ነበር፥ አበኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ስፍራ ባዶውን ነበረ። ሳኦልም፦ አንድ ነገር ሆኖአል፥ ንጹሕም አይደለም፥ በእውነት ንጹሕ አይደለም ብሎ አስቦአልና በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም። ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፥ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፦ የእሴይ ልጅ ትናንትና ወይም ዛሬ ግብር ሊበላ ያልመጣ ስለ ምን ነው? አለው። ዮናታንም ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ አጽንቶ ለመነኝ፥ እርሱም፦ ዘመዶቼ በከተማ ውስጥ መሥዋዕት አላቸውና፥ ወንድሜም ጠርቶኛልና እባክህ፥ አሰናብተኝ፥ አሁንም በዓይኖችህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ልሂድና ወንድሞቼን ልይ አለ፥ ስለዚህ ወደ ንጉሥ ሰደቃ አልመጣም ብሎ መለሰለት። የሳኦል ቁጣ በዮናታን ላይ ነደደና፦ አንተ የጠማማ ሴት ልጅ፥ የእሴይን ልጅ ለአንተ ማፈርያ ለእናትህም ኅፍረተ ሥጋ ማፈርያ እንደ መረጥህ እኔ አላውቅምን? የእሴይም ልጅ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ አንተና መንግሥትህ አትጸኑም፥ አሁንም የሞት ልጅ ነውና ልከህ አስመጣልኝ አለው። ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል፦ ስለ ምን ይሞታል? ያደረገውስ ምንድር ነው? ብሎ መለሰለት። ሳኦልም ሊወጋው ጦሩን ወረወረበት፥ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ፈጽሞ ሊገድለው እንደ ፈቀደ አወቀ። አባቱ ዳዊትን ስላሳፈረው ዮናታን ስለ ዳዊት አዝኖአልና እጅግ ተቆጥቶ ከሰደቃው ተነሣ፥ በመባቻውም በሁለተኛ ቀን ግብር አልበላም። እንዲህም ሆነ፥ በነጋው ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ወደ ሜዳ ወጣ፥ ከእርሱም ጋር ታናሽ ብላቴና ነበረ። ብላቴናውንም፦ ሮጠህ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልግልኝ አለው። ብላቴናውም በሮጠ ጊዜ ፍላጻውን ወደ ማዶ ወረወረው። ብላቴናውም ዮናታን ፍላጻውን ወደ ወረወረበት ስፍራ በመጣ ጊዜ ዮናታን፦ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ። ዮናታንም ደግሞ፦ ቶሎ ፍጠን፥ አትቆይ ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፥ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ። ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነገሩን ያውቁ ነበር እንጂ ብላቴናው ምንም አያውቅም ነበር። ዮናታንም መሣርያውን ለብላቴናው ሰጥቶ፦ ወደ ከተማ ውሰድ አለው። ብላቴናውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከስፍራው በደቡብ አጠገብ ተነሣ፥ በምድርም ላይ በግምባሩ ተደፋ፥ ሦስት ጊዜም ለሰላምታ ሰገደ፥ እየተላቀሱም እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ይልቁንም ዳዊት እጅግ አለቀስ። ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።

1 ሳሙኤል 20:18-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ ዮናታን እንዲህ አለው “ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት በዐል ነው፤ መቀመጫህ ባዶ ስለሚሆን በማእድ ላይ አለመኖርህ ይታወቃል፤ ከነገ ወዲያ ወደ ማታ ጊዜ ከዚህ በፊት ይህ ችግር ሲጀመር ወደ ተደበቅህበት ቦታ ሄደህ ከኤጼል ድንጋይ በስተጀርባ ተሸሸግ፤ እኔም ወደ ጎኑ ዒላማ በማስመሰል ሦስት ፍላጻዎችን እወረውራለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍላጻዎቹን እንዲያመጣ ልጁን እልካለሁ፤ ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወደዚህ ናቸውና አምጣቸው!’ ካልሁት አንተ ከተደበቅኽበት ቦታ ልትወጣ ትችላለህ፤ ስለዚህ ምንም ችግር እንደማይደርስብህና ምንም አደጋ እንደሌለ በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለሁ። ነገር ግን ልጁን እነሆ! ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወዲያ ናቸው!’ ያልኩት እንደ ሆነ እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። እርስ በርሳችን የገባነውን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደምንጠብቀው እግዚአብሔር ምስክራችን ነው። ” ስለዚህም ዳዊት በዱር ተደብቆ ቈየ፤ አዲስ ጨረቃ በምትታይበት በዓል ሳኦል ግብሩን ለማብላት ተቀመጠ፤ ከግድግዳው ጥግ በተለመደው የክብር ስፍራ ሲቀመጥ፥ አበኔር ከእርሱ ቀጥሎ ተቀመጠ፤ ዮናታንም በንጉሡ ፊት ለፊት ተቀምጦ ነበር፤ በዚህ ጊዜ የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሳኦል በዚያን ቀን ምንም ቃል አልተናገረም፤ ሳኦል ስለ ዳዊት ሲያስብ “ምናልባት አንድ ነገር ገጥሞት ይሆናል፤ ወይም በሕጉ መሠረት በሥርዓት አልነጻም ይሆናል” በማለት ያሰላስል ነበር፤ አዲስ ጨረቃ የታየችበት በዓል ካለፈ በኋላም በተከታዩ ቀን የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ስለዚህ ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፥ ዛሬም ወደዚህ ግብዣ ያልመጣው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ወደ ቤተልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ፤ ‘የእኛ ቤተሰብ በከተማው ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያቀርብና ወንድሜም በዚያ እንድገኝ ስላዘዘኝ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ እባክህ ፍቀድልኝና ወንድሞቼን ለማየት ልሂድ’ ብሎ ጠይቆኝ ነበር፤ በዚህ ምክንያት በንጉሡ ግብር ላይ አልተገኘም።” የሳኦልም ቊጣ በዮናታን ላይ ነድዶ እንዲህ አለ፤ “አንተ የጠማማና የዐመፀኛ ሴት ልጅ! በራስህ ላይ ኀፍረትንና በእናትህም ላይ ውርደትን ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወዳጀትህን ደኅና አድርጌ ዐውቃለሁ! የእሴይ ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተና መንግሥትህ ጸንታችሁ ለመኖር እንደማትችሉ አታውቅምን? አሁን ሄደህ አምጣው! እርሱ በሞት መቀጣት አለበት!” ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። ከዚህም የተነሣ ዮናታንን ለመግደል የያዘውን ጦር ወረወረበት፤ ስለዚህም ዮናታን አባቱ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቊርጥ ውሳኔ ማድረጉን አረጋገጠ፤ ዮናታንም በቊጣ ከማእዱ ላይ ተነሣ፤ በዚያ ቀን ማለትም አዲስ ጨረቃ በታየችበት በዓል በሁለተኛ ቀን ምንም ምግብ አልበላም፤ ሳኦል ዳዊትን በማዋረዱ ምክንያት ስለ ዳዊት ሁኔታ ዮናታን በብርቱ አዝኖ ነበር። በማግስቱ ጠዋት በቀጠሮአቸው መሠረት ዮናታን ዳዊትን ለማግኘት ወደ ሜዳ ሄደ፤ ሲሄድም አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ ነበር፤ ልጁንም “ፈጥነህ ሂድና የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ፈልገህ አምጣልኝ” አለው፤ ልጁም ሲሮጥ ዮናታን ከዚያ ልጅ ፊት አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ፤ ያም ልጅ ፍላጻው ባረፈበት ቦታ በደረሰ ጊዜ ዮናታን “ፍላጻው አልፎህ ሄዶአል! እዚያ ዝም ብለህ አትቁም! ፈጠን በል!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻውን አንሥቶ ወደ ጌታው ተመለሰ፤ ይህን ምሥጢር የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ እንጂ ልጁ ምንም አያውቅም ነበር። ዮናታንም ያንን ልጅ “መሣሪያዎቼን ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። ልጁም ከሄደ በኋላ ዳዊት ከድንጋዩ ቊልል በስተኋላ ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቶ በጒልበቱ በመንበርከክ ሦስት ጊዜ ወደ መሬት ሰገደ፤ እርሱና ዮናታን በሚሳሳሙበት ጊዜ ሁለቱም ያለቅሱ ነበር፤ ከዮናታንም ይልቅ የዳዊት ሐዘን የበረታ ነበር። ከዚህ በኋላ ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “በሰላም ሂድ፤ እኔና አንተ በዘሬና በዘርህ መካከል እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል።” ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።

1 ሳሙኤል 20:18-42 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ነገ የወር መባቻ በዓል ነው፤ መቀመጫህ ባዶ ስለሚሆን፥ አለመኖርህ ይታወቃል። ከነገ ወዲያ ምሽት ላይ ይህ ችግር በተፈጠረ ዕለት ወደ ተደበቅህበት ስፍራ ሂድና ኤጼል በተባለው ድንጋይ አጠገብ ቆይ። እኔም በአንድ ዒላማ ላይ እንደሚያነጣጥር ሰው ወደ ድንጋዩ አጠገብ ሦስት ፍላጻ እወረውራለሁ፤ ከዚያም፥ ‘ሂድና ፍላጾቹን አምጣቸው’ ብዬ አንድ ልጅ እልካለሁ፤ ልጁንም፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት፥ ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ሄደህ አምጣቸው’ ያልሁት እንደሆነ፥ በሕያው ጌታ ስም! ክፉ ነገር አያገኝህም፤ ውጣና ና፤ አደጋ እንደማይኖርም እምልልሃለሁ። ነገር ግን ልጁን፥ ‘እነሆ፤ ፍላጾቹ ያሉት ከአንተ ወዲያ ዐልፎ ነው’ ያልሁት እንደሆነ ጌታ እንድትሄድ ፈቅዷልና ሂድ። አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ ጌታ በመካከላችን ለዘለዓለም ምስክር ነው።” ስለዚህም ዳዊት በዱር ተደበቀ፤ የወር መባቻ በዓል በተከበረበት ጊዜ፥ ንጉሡ ግብር ለመብላት ተቀመጠ፤ ንጉሡ እንደ ወትሮው በግድግዳው አጠገብ ተቀመጠ፤ ዮናታን ከፊት ለፊቱ፥ አበኔር ደግሞ ከአጠገቡ ተቀመጡ፤ የዳዊት መቀመጫ ግን ባዶ ነበር። ሳኦልም፥ “ዳዊት በሥርዓቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በእርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፥ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም። በማግስቱም፥ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፥ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ዮናታንም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ዳዊት ወደ ቤተልሔም እንዲሄድ እፈቅድለት ዘንድ አጥብቆ ለመነኝ። እርሱም ‘ቤተሰባችን በከተማዪቱ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያደርግ በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛልና ልሂድ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ወንድሞቼን ለማየት እንድሄድ አሰናብተኝ’ አለኝ። በንጉሡ ግብር ላይ ሳይገኝ የቀረውም በዚህ ምክንያት ነው።” ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቆጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አንተ የዚያች ጠማማና ዐመፀኛ ሴት ልጅ! ለአንተው ለራስህ ውርደት፥ ለወላጅ እናትህም ዕፍረት ከሚሆነው ከእሴይ ልጅ ጋር መግጠምህን የማላውቅ መሰለህ? የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንህ መንግሥትህ አትጸኑም። መሞት ስለሚገባው፥ ሰው ላክና አስመጣልኝ!” ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል “ስለምን ይሞታል? ምንስ አደረገ?” ሲል መለሰ። ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፥ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሣቱን ዐወቀ። ዮናታንም በታላቅ ቁጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም። በማግስቱ ጠዋት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፥ ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤ ልጁንም፥ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፥ ከእርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ። ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፥ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው። እርሱም “ቶሎ በል! ፍጠን! አትቁም!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው ተመለሰ። ከዮናታንና ከዳዊት በስተቀር ልጁ ስለዚህ ነገር የሚያውቀው አንዳች አልነበረም። ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያውን ለልጁ ሰጥቶ፥ “ይዘህ ወደ ከተማ ተመለስ” አለው። ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር። ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።