1 ሳሙኤል 2:6-8
1 ሳሙኤል 2:6-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፤ ያወጣልም። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፤ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፤ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።
1 ሳሙኤል 2:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም። እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል። እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከመኳንንቱ ጋራ ያስቀምጣቸዋል፤ የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።
1 ሳሙኤል 2:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፥ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፥ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፥ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ።