1 ሳሙኤል 1:1-6

1 ሳሙኤል 1:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ከአ​ር​ማ​ቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የና​ሲብ ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤ​ልዩ ልጅ ፥ የኢ​ያ​ር​ም​ያል ልጅ፥ ኤፍ​ራ​ታ​ዊው ሕል​ቃና ነበረ። ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም። ያም ሰው በሴሎ ይሰ​ግድ ዘንድ፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ከከ​ተ​ማው ከአ​ር​ማ​ቴም በየ​ዓ​መቱ ይወጣ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ በዚያ ነበሩ። ሕል​ቃ​ናም የሚ​ሠ​ዋ​በት ቀን በደ​ረሰ ጊዜ ለሚ​ስቱ ለፍ​ና​ናና ለል​ጆ​ችዋ ሁሉ ዕድል ፋን​ታ​ቸ​ውን ሰጣ​ቸዉ። ለሐ​ናም ልጅ ስላ​ል​ነ​በ​ራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕል​ቃ​ናም ከዚ​ያ​ች​ኛ​ይቱ ይልቅ ሐናን ይወ​ድድ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግቶ ነበር። እንደ መከ​ራ​ዋና እንደ ኀዘ​ን​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አል​ሰ​ጣ​ትም ነበር። ስለ​ዚ​ህም ታዝን ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግ​ት​ዋ​ልና፥ ልጆ​ች​ንም አል​ሰ​ጣ​ት​ምና።

1 ሳሙኤል 1:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራማ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ የሚኖር ትውልዱ ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ ሕልቃና ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ የኤሊሁ የልጅ ልጅ ሲሆን፥ ኤሊሁ ደግሞ የቶሑ ልጅ የጹፍ የልጅ ልጅ ነበር፤ ሕልቃናም ሐናና ፍኒና ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ፍኒና ልጆች ነበሩአት፤ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም፤ ሕልቃና በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር፤ በዚያም ዘመን ሖፍኒና ፊንሐስ ተብለው የሚጠሩት የዔሊ ልጆች የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው በሴሎ ያገለግሉ ነበር። ሕልቃና መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ጊዜ ሁሉ ከመሥዋዕቱ ሥጋ አንድ ድርሻ ለጵኒና ይሰጣል፤ እንዲሁም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችዋ ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ ድርሻ ያድላል፤ ሐናን ይወዳት ስለ ነበር እጥፍ ድርሻ ይሰጣት ነበር፤ ቢሆንም እግዚአብሔር ልጅ ስላልሰጣት መኻን ነበረች፤ እግዚአብሔርም ልጅ ስላልሰጣት ጣውንትዋ ጵኒና ሐናን የሚያስቈጣ ነገር በመፈለግ ታበሳጫት ነበር፤