1 ነገሥት 9:1-28
1 ነገሥት 9:1-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን የወደደውን የልቡን አሳብ ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን እንደ ተገለጠለት ዳግመኛ ተገለጠለት። እግዚአብሔርም አለው “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ፍርዴንም ብትጠብቅ፥ እኔ ‘ከእስራኤል ዙፋን ከዘርህ ሰው አታጣም፤’ ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ። እናንተና ልጆቻችሁ ግን እኔን ከመከትል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ትእዛዜንና ሥርዐቴን ባትጠብቁ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ምሳሌና ተረት ይሆናሉ። ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል። መልሰውም ‘ከግብጽ ምድር አባቶቻቸውን ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው፤’ ይላሉ።” ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች የሠራበት ሃያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው። የጢሮስም ንጉሥ ኪራም የሚሻውን ያህል የዝግባና የጥድ እንጨት የሚሻውንም ያህል ወርቅ ሁሉ ለሰሎሞን ሰጥቶት ነበር። ኪራምም ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ያይ ዘንድ ከጢሮስ ወጣ፤ ደስም አላሰኙትም። እርሱም “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድር ናቸው?” አለ። እስከ ዛሬም ድረስ የከቡል አገር ተብለው ተጠሩ። ኪራምም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ለንጉሡ ላከ። ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት፥ ሚሎንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ ሐጾርንም፥ መጊዶንም፥ ጌዝርንም ይሠራ ዘንድ ገባሮችን መልምሎ ነበር። የግብጽም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጌዝርን ይዞ ነበር፤ በእሳትም አቃጥሎ ነበር፤ በከተማም የኖሩትን ከነዓናውያን ገድሎ ነበር፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር። ሰሎሞንም ጌዝርን፥ የታችኛውንም ቤት ሖሮን፥ ባዕላትንም፥ በምድረ በዳም አገር ያለችውን ተድሞርን፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ። ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞራውያንና ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከሒዋውያንና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን፥ የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ በኋላቸው የቀሩትን ልጆቻቸውን፥ ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው። ሰሎሞንም ከእስራኤል ልጆች ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ እነርሱ ግን ሰልፈኞች ሎሌዎችም፥ መሳፍንትም፥ አለቆችም፥ የሠረገሎችና የፈረሶች ባልደራሶች ነበሩ። ሰሎሞንም በሚሠራው ሥራ ላይ ሠራተኛውን ሕዝብ የሚያዝዙ አለቆች አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። የፈርዖንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤትዋ ወጣች፤ በዚያን ጊዜም ሚሎን ሠራ። ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የደኅንነቱን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔር ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ። ንጉሡም ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር በኤርትራ ባሕር ዳር በኤሎት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦች ሠራ። ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን ባሪያዎች ጋር የባሕሩን ነገር የሚያውቁ መርከበኞች ባሪያዎቹን ሰደደ። ወደ ኦፊርም መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን ይዘው መጡ።
1 ነገሥት 9:1-28 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚህም በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን ያደርገው ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን እንደ ተገለጠለት ዳግመኛ ተገለጠለት። እግዚአብሔርም አለው፥ “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ እንደ ጸሎትህም ሁሉ አደረግሁልህ፤ ለዘለዓለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖችና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። ዳዊትም አባትህ በጽድቅ፥ በንጹሕ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ሕጌንም ብትጠብቅ፥ እኔ፦ በእስራኤል ላይ የሚገዛ ሰውን ከአንተ አላጠፋም ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጸናለሁ። ነገር ግን እናንተና ልጆቻችሁ እኔን ትታችሁ ወደ ኋላ ብትመለሱ ለሙሴ በፊታችሁ የሰጠሁትን ትእዛዜንና ሥርዐቴን ባትጠብቁ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ። ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል። መልሰውም፦ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት አባቶቻቸውን ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው ይላሉ።” ያንጊዜም ሰሎሞን የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠራው ቤት አስገባት። ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች በሠራበት በሃያ ዓመት ውስጥ፥ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም በዝግባና በጥድ እንጨት፥ በወርቅና በሚሻውም ሁሉ ሰሎሞንን ረድቶት ነበር። ያንጊዜም ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው። ኪራምም ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ያይ ዘንድ ከጢሮስ ወጣ፤ ወደ ገሊላም ሄደ፤ ደስም አላሰኙትም። እርሱም አለው፥ “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድን ናቸው?” እስከ ዛሬም ድረስ ወሰን ብሎ ጠራቸው። ኪራምም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ለሰሎሞን አመጣ። ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር። የግብፅም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጋዜርን ያዘ፤ በእሳትም አቃጠላት፤ በሜርጎብ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንንም ገደላቸው፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት እነዚያን አገሮች ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር። ሰሎሞንም ጋዜርንና የታችኛውን ቤቶሮንን፥ ባዕላትንም ሠራ፤ በምድረ በዳ ሀገር ያለችውን ኤያቴርሞትን ሠራ፤ ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፤ የሰረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም፥ በሊባኖስም፥ በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ። ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞሬዎናውያንና ከኬጤዎናውያን፥ ከከናኔዎን፥ ከፌርዜዎናውያን፥ ከኤዌዎናውያን፥ ከኢያቡሴዎናውያንና ከጌርጌሴዎናውያን፥ የቀሩትን አሕዛብ ሁሉ፥ ከእነርሱም በኋላ በምድሪቱ የቀሩትን፥ የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው። ሰሎሞንም ከእስራኤል ልጆች ማንንም ገባር አላደረገም፤ እነርሱ ግን ተዋጊዎች፥ ሎሌዎችም፥ መሳፍንትም፥ አለቆችም፥ የሰረገሎችና የፈረሶች ባልደራሶች ነበሩ። ሰሎሞንም በሚሠራው ሥራ ላይ ሠራተኛውን ሕዝብ የሚያዝዙ አለቆች አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። የፈርዖንንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤቷ አመጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎንን ሠራት። ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የሰላሙን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ። ንጉሡም ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር በኤርትራ ባሕር ዳር በኤላት አጠገብ ባለችው በጋሴዎንጋቤር መርከቦችን ሠራ። ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ባሕሩን መቅዘፍ የሚያውቁ መርከበኞች አገልጋዮቹን ላከ። ወደ አፌርም ደረሱ፤ ከዚያም አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞንም ይዘው አገቡ።
1 ነገሥት 9:1-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን ሠርቶ ከጨረሰና ለመሥራት የፈለገውንም ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣ እግዚአብሔር ለሰሎሞን በገባዖን ተገልጦለት እንደ ነበረ ሁሉ ዳግም ተገለጠለት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በፊቴ ያቀረብኸውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ ይህን የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ፣ ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ቀድሼዋለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ። “አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በልበ ቅንነትና በትክክለኛነት በፊቴ ብትሄድ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ ሥርዐቶቼንና ሕጎቼን ብትጠብቅ፣ ለአባትህ ለዳዊት፣ ‘በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዘርህ አታጣም’ በማለት በሰጠሁት ተስፋ መሠረት ዙፋንህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ። “ነገር ግን አንተም ሆንህ ልጆችህ እኔን ከመከተል ወደ ኋላ ብትመለሱ፣ የሰጠኋችሁን ትእዛዞችና ሥርዐቶች ሳትጠብቁ ብትቀሩ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣ እኔም እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላቸዋለሁ፤ ስለ ስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስም እተወዋለሁ፤ ከዚያም እስራኤል በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ይሆናሉ፤ ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም እንኳ፣ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ እያፌዘም፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤ ሰዎቹም መልሰው፣ ‘አዎን እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎች አማልክትን በመከተል ስላመለኳቸውና ስላገለገሏቸው ነው’ ይላሉ።” ሰሎሞን ሁለቱን ሕንጻዎች፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የንጉሡን ቤተ መንግሥት ሠርቶ በፈጸመበት በሃያኛው ዓመት መጨረሻ፣ ንጉሥ ሰሎሞን በገሊላ የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም ሰጠው፤ ንጉሡ ይህን ያደረገውም፣ የሚያስፈልገውን ሁሉ ዝግባ፣ ጥድና ወርቅ ኪራም ሰጥቶት ስለ ነበር ነው፤ ይሁን እንጂ ኪራም ከጢሮስ ተነሥቶ ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት በሄደ ጊዜ አልተደሰተባቸውም፤ እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም “ከቡል ምድር” አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ። በዚያ ጊዜ ኪራም ለንጉሡ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ልኮለት ነበር። ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ በጌዝር ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ አቃጠላትም፤ ነዋሪዎቿን ከነዓናውያንን ገድሎ ለልጁ ለሰሎሞን ሚስት መዳሪያ አድርጎ ሰጥቷት ነበር፤ ሰሎሞንም ጌዝርን መልሶ ሠራት፤ እንዲሁም የታችኛውን ቤትሖሮንን፣ ባዕላትን፣ በይሁዳ ምድር በምድረ በዳው የምትገኘውን ተድሞርን ሠራ፤ በአጠቃላይ ሰሎሞን በኢየሩሳሌም፣ በሊባኖስና በግዛቶቹ ሁሉ ለመሥራት የፈለጋቸውን ነገሮች፣ ዕቃ የሚከማችባቸውን ከተሞች፣ እንዲሁም ሠረገለኞችና ፈረሰኞች የሚቀመጡባቸውን ከተሞች ሁሉ ሠራ። እስራኤላውያን ያልሆኑትን ከአሞራውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን የተረፉትን ሕዝቦች ሁሉ፣ እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው። ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ ይልቁንም እነርሱ ወታደሮቹ፣ ሹማምቱ፣ የጦር አዛዦቹ፣ ሻምበሎቹ፣ የፈረሰኞችና የሠረገለኞች አዛዦቹ ነበሩ። እነዚህም ሰሎሞን የሚያሠራውን ሥራ የሚያከናውኑትን ሠራተኞች የሚቈጣጠሩ አለቆች ናቸው፤ ቍጥራቸውም ዐምስት መቶ ዐምሳ ነበር። የፈርዖን ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከመጣች በኋላ ሰሎሞን ሚሎንን ሠራ። ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ በዓመት ሦስት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በማቅረብ፣ ከዚሁ ጋራ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም የቤተ መቅደሱን ግዳጅ ተወጣ። እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ጠረፍ፣ በኤላት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋራ ዐብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ። እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።
1 ነገሥት 9:1-28 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን የወደደውን የልቡን አሳብ ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በገባዖን ለሰሎሞን እንደ ተገለጠለት ዳግመኛ ተገለጠለት። እግዚአብሔርም አለው “በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፤ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ። ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ፍርዴንም ብትጠብቅ፥ እኔ ‘ከእስራኤል ዙፋን ከዘርህ ሰው አታጣም፤’ ብዬ ለአባትህ ለዳዊት እንደ ተናገርሁ፥ የመንግሥትህን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ። እናንተና ልጆቻችሁ ግን እኔን ከመከትል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ትእዛዜንና ሥርዐቴን ባትጠብቁ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ምሳሌና ተረት ይሆናሉ። ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል። መልሰውም ‘ከግብጽ ምድር አባቶቻቸውን ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው፤’ ይላሉ።” ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት ሁለቱን ቤቶች የሠራበት ሃያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው። የጢሮስም ንጉሥ ኪራም የሚሻውን ያህል የዝግባና የጥድ እንጨት የሚሻውንም ያህል ወርቅ ሁሉ ለሰሎሞን ሰጥቶት ነበር። ኪራምም ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ያይ ዘንድ ከጢሮስ ወጣ፤ ደስም አላሰኙትም። እርሱም “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ እነዚህ ከተሞች ምንድር ናቸው?” አለ። እስከ ዛሬም ድረስ የከቡል አገር ተብለው ተጠሩ። ኪራምም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ለንጉሡ ላከ። ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት፥ ሚሎንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ ሐጾርንም፥ መጊዶንም፥ ጌዝርንም ይሠራ ዘንድ ገባሮችን መልምሎ ነበር። የግብጽም ንጉሥ ፈርዖን ወጥቶ ጌዝርን ይዞ ነበር፤ በእሳትም አቃጥሎ ነበር፤ በከተማም የኖሩትን ከነዓናውያን ገድሎ ነበር፤ ለልጁም ለሰሎሞን ሚስት ትሎት አድርጎ ሰጥቶአት ነበር። ሰሎሞንም ጌዝርን፥ የታችኛውንም ቤት ሖሮን፥ ባዕላትንም፥ በምድረ በዳም አገር ያለችውን ተድሞርን፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ይሠራ ዘንድ የወደደውን ሁሉ ሠራ። ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞራውያንና ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከሒዋውያንና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን፥ የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ በኋላቸው የቀሩትን ልጆቻቸውን፥ ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው። ሰሎሞንም ከእስራኤል ልጆች ማንንም ባሪያ አላደረገም፤ እነርሱ ግን ሰልፈኞች ሎሌዎችም፥ መሳፍንትም፥ አለቆችም፥ የሠረገሎችና የፈረሶች ባልደራሶች ነበሩ። ሰሎሞንም በሚሠራው ሥራ ላይ ሠራተኛውን ሕዝብ የሚያዝዙ አለቆች አምስት መቶ አምሳ ነበሩ። የፈርዖንም ልጅ ከዳዊት ከተማ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ወደ ቤትዋ ወጣች፤ በዚያን ጊዜም ሚሎን ሠራ። ሰሎሞንም በየዓመቱ ሦስት ጊዜ የሚቃጠለውንና የደኅንነቱን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሠራው መሠዊያ ላይ ያሳርግ ነበር፤ በእግዚአብሔር ፊት ባለው መሠዊያ ላይ ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ ቤቱንም ጨረሰ። ንጉሡም ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር በኤርትራ ባሕር ዳር በኤሎት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦች ሠራ። ኪራምም በእነዚያ መርከቦች ከሰሎሞን ባሪያዎች ጋር የባሕሩን ነገር የሚያውቁ መርከበኞች ባሪያዎቹን ሰደደ። ወደ ኦፊርም መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሰሎሞን ይዘው መጡ።
1 ነገሥት 9:1-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገለጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት። “በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ። አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥ ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ። ነገር ግን አንተ ወይም ዘሮችህ እኔን መከተል ትታችሁ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትፈጽሙና ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ፥ እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል። ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል። ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።” ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ኻያ ዓመት ነበር፤ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞች ለኪራም ሰጠው፤ ኪራምም ሄዶ ከተሞቹን አየ፤ ነገር ግን ደስ አላሰኙትም፤ ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል፤ ኪራም ለሰሎሞን የላከለት ወርቅ አራት ሺህ ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን ነበር። ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጒልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ። ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፥ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቊጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ሴት ልጁን ለሰሎሞን በዳረለት ጊዜ የጌዜርን ከተማ ማጫ አድርጎ ሰጣት፤ ሰሎሞንም ጌዜርንና የታችኛውን ቤትሖሮን እንደገና አሠራ። ባዕላት፥ በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ፤ እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ። ለሰሎሞን የጒልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ ያልገደሉአቸው የከነዓን ሕዝብ ትውልዶች ነበሩ፤ እነዚህም ትውልዶች እስከ አሁን ድረስ ባሪያዎች ሆነው የሚያገለግሉ አሞራውያን፥ ሒታውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ እነርሱ ባለሥልጣኖች፥ ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር። ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጒልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው። የግብጽ ንጉሥ ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ጐድጓዳ ስፍራ ተሞልቶ በመስተካከል እንዲሠራ አደረገ። ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዐይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ። እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት፤ እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
1 ነገሥት 9:1-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገለጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት። “በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ። አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥ ለአባትህ ለዳዊት ‘ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም’ በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ፥ ዙፋንህ በእስራኤል ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ። ነገር ግን አንተ ወይም ዘሮችህ እኔን መከተል ትታችሁ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትፈጽሙና ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ፥ እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል። ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል። ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ ጌታ አምላካቸውን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።” ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ኻያ ዓመት ነበር። የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው። ኪራምም ሄዶ ከተሞቹን አየ፤ ነገር ግን ደስ አላሰኙትም። ሰሎሞንን “ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች ለካ እነዚህ ናቸውን?” አለው፤ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ያ አካባቢ በሙሉ ካቡል እየተባለ ይጠራል። ኪራም ለሰሎሞን የላከለት ወርቅ አራት ሺህ ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን ነበር። ለሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ የኢየሩሳሌምን ቅጽር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጐድጓዳ ስፍራ ሞልተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ለመሥራት የሚገደዱ ሠራተኞች ነበሩ፤ እንዲሁም ሐጾር፥ መጊዶና ጌዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችንም እንዲሠሩለት አደረገ። ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፥ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ሴት ልጁን ለሰሎሞን በዳረለት ጊዜ የጌዜርን ከተማ ማጫ አድርጎ ሰጣት። ሰሎሞንም ጌዜርንና የታችኛውን ቤትሖሮን እንደገና አሠራ። ባዕላት፥ በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ። እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ። ከእስራኤል ሕዝብ ያልሆኑትን ከአሞራውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤው ያውንና ከኢያቡሳውያን ሕዝቦች ሁሉ የተረፉትን፥ እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን እነዚህን እስከ ዛሬ እንደሚደረገው ሁሉ፥ ሰሎሞን ለግዳጅ ሥራ መለመላቸው። ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባርያ አድርጎ አላሠራም፤ እነርሱ ባለ ሥልጣኖች፥ ወታደሮች፥ የጦር መኰንኖች፥ የጦር አዛዦች፥ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኀላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር። ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኀምሳ ኀላፊዎች ነበሩአቸው። የግብጽ ንጉሥ ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን ከከተማይቱ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን ጐድጓዳ ስፍራ ተሞልቶ በመስተካከል እንዲሠራ አደረገ። ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዓይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ። እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት። እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።