1 ነገሥት 19:19-21
1 ነገሥት 19:19-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት። ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው። ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።
1 ነገሥት 19:19-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ኤልያስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬ አውጥቶ ራሱ በዐሥራ ሁለተኛው ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ መጥቶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት። ከዚያም ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ኤልያስን ተከትሎ እየሮጠ፣ “አባቴንና እናቴን ስሜ እንድሰናበታቸው ፍቀድልኝ፤ ከዚያም እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ ምን ያደረግሁህ ነገር አለ? ልትመለስ ትችላለህ” አለው። ስለዚህም ኤልሳዕ ትቶት ተመለሰ። ሁለቱን በሬዎቹን ወስዶ ዐረደ፤ የዕርሻ ዕቃውን አንድዶ ሥጋቸውን በመቀቀል ለሕዝቡ ሰጠ፤ እነርሱም በሉ። ከዚያም ኤልያስን ለመከተል ሄደ፤ ረዳቱም ሆነ።
1 ነገሥት 19:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጎናጸፊያውን ጣለበት። በሬዎቹንም ተወ፤ ከኤልያስም በኋላ ሮጦ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ፤” አለው። እርሱም “ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው። ከእርሱም ዘንድ ተመልሶ ሁለቱን በሬዎች ወስዶ አረዳቸው፤ ሥጋቸውንም በበሬዎቹ ዕቃ ቀቀለው፤ ለሕዝቡም ሰጣቸው፤ በሉም፤ እርሱም ተነሥቶ ኤልያስን ተከትሎ ሄደ፤ ያገለግለውም ነበር።
1 ነገሥት 19:19-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኤልያስ ከዚያ ከሄደ በኋላ የዮሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ሁለት በሬዎች ጠምዶ ሲያርስ አገኘው፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ በዐሥራ አንድ ጥማድ በሬዎች የሚያርሱ ደቦኞች ነበሩ፤ ኤልሳዕም በመጨረሻው ዐሥራ ሁለተኛ ጥማድ ያርስ ነበር፤ ኤልያስም መጐናጸፊያውን አውልቆ በኤልሳዕ ላይ ደረበለት። በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት። ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ ዐረዳቸው፤ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ።
1 ነገሥት 19:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)