1 ዮሐንስ 4:1-6

1 ዮሐንስ 4:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ። የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይታችሁ የምታውቁት በዚህ ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የሚያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የማያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም፤ ይህም መንፈስ ይመጣል ሲባል የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው፤ እርሱ አሁን እንኳ በዓለም ላይ አለ። ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል። ሐሰተኞች ነቢያት የዓለም ናቸው፤ የሚናገሩትም የዓለምን ነገር ነው። ዓለምም እነርሱን ይሰማቸዋል። እኛ የእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ሁሉ ይሰማናል፤ የእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። እውነተኛን መንፈስና ሐሰተኛን መንፈስ ለይተን የምናውቀው በዚህ ነው።

1 ዮሐንስ 4:1-6

1 ዮሐንስ 4:1-6 NASV