1 ቆሮንቶስ 7:1-24

1 ቆሮንቶስ 7:1-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ስለ ጻፋ​ች​ሁ​ል​ኝስ ለሰው ወደ ሴት አለ​መ​ቅ​ረብ ይሻ​ለ​ዋል። ነገር ግን እን​ዳ​ት​ሴ​ስኑ ሰው ሁሉ በሚ​ስቱ ይወ​ሰን፤ ሴትም ሁላ በባ​ልዋ ትወ​ሰን። ለሚ​ስ​ትም ባልዋ የሚ​ገ​ባ​ትን ያድ​ር​ግ​ላት፤ እን​ዲሁ ሚስ​ትም ለባ​ልዋ የሚ​ገ​ባ​ውን ታድ​ር​ግ​ለት። ሚስት በራ​ስዋ አካል ሥል​ጣን የላ​ትም፤ ሥል​ጣን ለባ​ልዋ ነው እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ባል በራሱ አካል ሥል​ጣን የለ​ውም፤ ሥል​ጣን ለሚ​ስቱ ነው እንጂ። ለጸ​ሎት እን​ድ​ት​ተጉ ከም​ት​ስ​ማ​ሙ​በት ጊዜ ብቻ በቀር፥ ባልና ሚስት አት​ለ​ያዩ፤ ዳግ​መኛ ሰይ​ጣን ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጋ​ችሁ በአ​ን​ድ​ነት ኑሩ፤ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ደካማ ነውና ። ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ እንደ ፈቃድ ነው እንጂ፥ ላዝ​ዛ​ችሁ አይ​ደ​ለም። ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወ​ዳ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እን​ዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆ​ነም አለና። ነገር ግን ያላ​ገ​ቡ​ት​ንና አግ​ብ​ተው የፈ​ቱ​ትን እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ ይሻ​ላ​ቸ​ዋል እላ​ለሁ። መታ​ገሥ ባይ​ችሉ ግን ያግቡ፤ በፍ​ት​ወት ከመ​ቃ​ጠል ማግ​ባት ይሻ​ላ​ልና። ያገ​ቡ​ት​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በራሴ ትእ​ዛ​ዝም አይ​ደ​ለም፤ ሚስ​ትም ከባ​ልዋ አት​ፋታ። ከተ​ፋ​ታ​ችም ብቻ​ዋን ትኑር፤ ያለ​ዚያ ከባ​ልዋ ጋር ትታ​ረቅ፤ ባልም ሚስ​ቱን አይ​ፍታ። ሌላ​ውን ግን ከራሴ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከጌ​ታ​ች​ንም አይ​ደ​ለም፤ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል የማ​ታ​ምን፥ ባል​ዋ​ንም የም​ታ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ሱም ጋር ለመ​ኖር የም​ት​ወድ ሚስት ያለ​ችው ሰው ቢኖር ሚስ​ቱን አይ​ፍታ። ሴቲ​ቱም የማ​ያ​ም​ንና ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ፈ​ቅር ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ሊኖር የሚ​ወድ ባል ቢኖ​ራት ባል​ዋን አት​ፍታ። የማ​ያ​ምን ባል በሚ​ስቱ ይቀ​ደ​ሳ​ልና፤ የማ​ታ​ምን ሚስ​ትም በባ​ልዋ ትቀ​ደ​ሳ​ለ​ችና፤ ያለ​ዚ​ያማ ልጆ​ቻ​ቸው ርኩ​ሳን ይሆ​ናሉ፤ አሁን ግን ቅዱ​ሳን ናቸው። የማ​ያ​ምን ግን ቢፈታ ይፍታ፤ ወን​ድ​ምና እኅት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ላም ስለ ጠራ​ቸው እን​ደ​ዚህ ላለ ግብር አይ​ገ​ዙ​ምና። ሚስ​ትም ባል​ዋን ታድ​ነው እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና፤ ባልም ሚስ​ቱን ያድ​ናት እንደ ሆነ አያ​ው​ቅ​ምና። ነገር ግን ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው፥ ሁሉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠራው እን​ዲሁ ይኑር፤ ለአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትም ሁሉ እን​ዲህ ሥር​ዐት እን​ሠ​ራ​ለን። ተገ​ዝሮ ሳለ የተ​ጠራ ቢኖር አለ​መ​ገ​ዘ​ርን አይ​መኝ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረም ቢጠራ ከዚያ ወዲያ አይ​ገ​ዘር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም። ሁሉ እንደ ተጠራ እን​ዲሁ ይኑር። አንተ ባርያ ሳለህ ብታ​ምን አያ​ሳ​ዝ​ንህ፤ የሚ​ቻ​ልህ ከሆነ ግን ነጻ​ነ​ት​ህን አግኝ። የተ​ጠራ ባሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነጻ​ነት ያለው ነውና፤ እን​ዲሁ ነጻ​ነት ያለ​ውም ከተ​ጠራ የክ​ር​ስ​ቶስ ባርያ ነው። በዋጋ ገዝ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና የሰው ተገ​ዦች አት​ሁኑ። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ች​ሁም በተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኑሩ።

1 ቆሮንቶስ 7:1-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስለ ጻፋችሁልኝ ጕዳይ፣ ሰው ወደ ሴት ባይደርስ መልካም ነው፤ ነገር ግን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዷም ሴት የራሷ ባል ይኑራት። ባል ለሚስቱ የሚገባትን ሁሉ ያድርግላት፤ ሚስትም ለባሏ እንዲሁ። ሚስት በራሷ አካል ላይ ሥልጣን የላትም፤ ባሏ እንጂ። እንዲሁም ባል በራሱ አካል ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሚስቱ እንጂ። በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፣ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ባለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደ ገና ዐብራችሁ ሁኑ። ይህን የምለው ግን እንደ ትእዛዝ ሳይሆን እንደ ምክር ነው። ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ምኞቴ ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከእግዚአብሔር የተቀበለው የራሱ የሆነ ስጦታ አለው፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው። ላላገቡና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ግን እንዲህ እላለሁ፤ ሳያገቡ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው። ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ፤ በምኞት ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና። ላገቡት ይህን ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም። ሚስት ከባሏ አትለያይ፤ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር፤ አለዚያ ከባሏ ጋራ ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን አይፍታት። ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህንም የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም። ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም ቢኖርና ሚስቱ ዐብራው ለመኖር የምትፈቅድ ከሆነ፣ ሊፈታት አይገባውም። ያላመነ ባል ያላት ሴት ብትኖርና እርሱም ዐብሯት ለመኖር የሚፈቅድ ከሆነ፣ ልትፈታው አይገባትም። ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሷልና፤ ያላመነችም ሚስት በሚያምን ባሏ ተቀድሳለች፤ አለዚያማ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። ነገር ግን የማያምነው ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ አንድ ወንድም ወይም እኅት በዚህ ሁኔታ የታሰሩ አይደሉም፤ እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው። አንቺ ሴት፤ ባልሽን ታድኚው እንደ ሆነ ምን ታውቂያለሽ? ወይስ አንተ ሰው፤ ሚስትህን ታድናት እንደ ሆነ ምን ታውቃለህ? ብቻ እያንዳንዱ ሰው ጌታ እንደ ወሰነለት፣ እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው በዚያው ይመላለስ። በአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ የምንደነግገው ይህንኑ ነው። አንድ ሰው ተገርዞ ሳለ ቢጠራ፣ እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን፤ ሳይገረዝም ተጠርቶ ከሆነ አይገረዝ። መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ ዋናው ነገር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸሙ ነው። እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ሁኔታ ጸንቶ ይኑር። በተጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርህን? በዚህ አትጨነቅ፤ ነጻነትህን ማግኘት ከቻልህ ግን ነጻነትህን ተቀበል። ምክንያቱም ባሪያ ሆኖ ሳለ በጌታ የተጠራ፣ የጌታ ነጻ ሰው ነው፤ እንዲሁም ሲጠራ ነጻ የነበረ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ ስለዚህ የሰው ባሮች አትሁኑ። ወንድሞች ሆይ፤ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋራ ጸንቶ ይኑር።

1 ቆሮንቶስ 7:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለ ጻፋችሁልኝስ ነገር፥ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው። ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት። ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ሁኑ። ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም። ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ። ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ። ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥ ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፥ እኔ ግን አላዝም፥ ጌታ እንጂ። ሌሎችንም እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፥ አትተወው። ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው። የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ። ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ። እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር። ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል። ባሪያ ሆኖ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። ወንድሞች ሆይ፥ እያንዳንዱ በተጠራበት እንደዚሁ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር።

1 ቆሮንቶስ 7:1-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለ ጻፋችሁልኝ ጥያቄ ሰው ከሴት ጋር ግንኙነት ባያደርግ መልካም ነው። ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ የራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት የራስዋ ባል ይኑራት። ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን የጋብቻ መብትዋን አይከልክላት፤ እንዲሁም ሚስት ለባልዋ ማድረግ የሚገባትን የጋብቻ መብቱን አትከልክለው። ሚስት በሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ በእርስዋ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያለው ባልዋ ነው። እንዲሁም ባል በሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ በእርሱ ሰውነት ላይ ሥልጣን ያላት ሚስቱ ነች። በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ። ይህን ግን የምላችሁ እንደምክር ነው እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም። ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሚስት ሳያገባ ቢኖር በወደድኩ ነበር፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር የተለየ ስጦታ ሰጥቶታል፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ፥ ሌላውም ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው። ላላገቡና እንዲሁም ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች የምለው እንዲህ ነው፤ ሳያገቡ እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ መልካም ነው። ነገር ግን በሥጋ ምኞት ከመቃጠል ይልቅ ማግባት የተሻለ ነውና ራሳቸውን መቈጣጠር ቢያቅታቸው ያግቡ። ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባልዋ አትለይ፤ ብትለይም ሳታገባ ለብቻዋ ትኑር፤ ወይም ከባልዋ ጋር ትታረቅ፤ እንዲሁም ባል ሚስቱን አይፍታ። ለሌሎቹ ግን ጌታ ሳይሆን እኔ ራሴ የምለው እንዲህ ነው፤ አንድ ክርስቲያን ሰው ክርስቲያን ያልሆነች ሚስት ብትኖረውና አብራው ለመኖር ብትፈልግ አይፍታት። ክርስቲያን ሴት ክርስቲያን ያልሆነ ባል ቢኖራትና አብሮአት ለመኖር ቢፈልግ አትፍታው። ክርስቲያን ያልሆነ ባል ክርስቲያን በሆነች ሚስቱ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ይሆናል፤ ክርስቲያን ያልሆነች ሚስትም ክርስቲያን በሆነው ባልዋ ምክንያት የእግዚአብሔር ወገን ትሆናለች፤ እንደዚህ ካልሆነማ ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ሊሆኑ አይችሉም፤ በዚህ ዐይነት ከኖራችሁ ግን ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ክርስቲያን ያልሆነ ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ በዚህ ጊዜ ግን ክርስቲያን የሆነው ወገን ባልም ሆነ ሚስት በምንም ዐይነት ግዴታ አይያዝም። እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው። አንቺ ክርስቲያን ሴት፥ ክርስቲያን ያልሆነውን ባልሽን ምናልባት ታድኚው እንደ ሆነ ምን ታውቂያለሽ? አንተስ ክርስቲያን ወንድ፥ ክርስቲያን ያልሆነች ሚስትህን ምንአልባት ታድናት እንደ ሆንክ ምን ታውቃለህ? እያንዳንዱ ጌታ በሰጠው ስጦታና እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የሰጠሁት መመሪያ ይህንኑ ነው። ማንም ሰው ከተገረዘ በኋላ የተጠራ ከሆነ እንዳልተገረዘ ለመሆን አያስብ፤ ሳይገረዝ የተጠራ ከሆነም መገረዝን አይፈልግ። መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ዋጋ የለውም፤ ዋናው ነገር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር። እግዚአብሔር በጠራህ ጊዜ ባሪያ ነበርክን? ብትሆንም ግድ የለም፤ አትጨነቅበት፤ ነጻ የመውጣት ዕድል ብታገኝ ግን ይህ ዕድል አያምልጥህ። ባሪያ ሆኖ ሳለ በጌታ የተጠራ ሰው በጌታ ነጻነትን አግኝቶአል፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ ሰው የክርስቶስ ባሪያ ነው። እግዚአብሔር በዋጋ ስለ ገዛችሁ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ። ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ እያንዳንዱ ሰው በተጠራበት ጊዜ በነበረበት ሁኔታ በእግዚአብሔር ጋር በዚያ ይኑር።

1 ቆሮንቶስ 7:1-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጻፋችሁልኝን ነገር በተመለከተ፥ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው። ነገር ግን ከዝሙት ለመራቅ እያንዳንዱ ወንድ ለራሱ ሚስት ትኑረው፤ እያንዳንዱዋም ሴት ለራስዋ ባል ይኑራት። ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስት ለባሏ። ሚስት በገዛ ሰውነቷ ላይ ሥልጣን የላትም፤ ሥልጣን ለባሏ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ። ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም። ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፤ አንዱ እንደዚህ ሌላውም እንደዚያ ዓይነት። ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤ ነገር ግን በመሻት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ካልቻሉ ያግቡ። ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባሏ አትለይ፤ ብትለይም ሳታገባ ለብቻዋ ትኑር፤ ወይም ከባሏ ጋር ትታረቅ፤ እንዲሁም ባል ሚስቱን አይፍታ። ሌሎችንም፥ ጌታም አይደለም፥ እኔ እላለሁ፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር፥ እርሷም ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ፥ አይፍታት፤ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርሷ ጋር ለመኖር ቢስማማ፥ አትተወው። ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፤ ያላመነችም ሚስት በባሏ ተቀድሳለች፤ እንደዚህ ካልሆነ ግን፥ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ እንደዚህ ከሆነ ግን የተቀደሱ ናቸው። የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ቢሆን ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል። ሚስት ሆይ! ባልሽን ታድኚ እንደሆን ምን ታውቂያለሽ? ወይስ ባል ሆይ! ሚስትህን ታድን እንደሆንህ ምን ታውቃለህ? እያንዳንዱ ጌታ በሰጠውና እግዚአብሔር በጠራው ጊዜ በነበረበት ሁኔታ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የሰጠሁት መመሪያ ይህ ነው። ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደሆነ፥ መገረዝን አይፈልግ። መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ምንም ማለት አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ። እያንዳንዱ ሲጠራ በነበረበት ሁኔታ ይኑር። ባርያ ሆነህ ተጠርተህ እንደሆነ አይገድህም፤ ነጻ ልትወጣ ቢቻልህ ግን ነጻነትን ተቀበል። ባርያ ሆኖ ሳላ በጌታ የተጠራ የጌታ ነጻ ነውና፤ እንዲሁም ነጻ ሆኖ ሳለ የተጠራ የክርስቶስ ባርያ ነው። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባርያዎች አትሁኑ። ወንድሞች ሆይ! እያንዳንዱ በተጠራ ጊዜ የነበረበት ሁኔታ ምንም ይሁን፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ይኑር።