1 ቆሮንቶስ 6:12-20

1 ቆሮንቶስ 6:12-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በሆ​ነው ሁሉ ላይ ሥል​ጣን አለኝ፤ ግን ሁሉ የሚ​ጠ​ቅ​መኝ አይ​ደ​ለም፤ ሁሉም ይቻ​ለ​ኛል፤ ነገር ግን በእኔ ላይ እን​ዲ​ሠ​ለ​ጥን የማ​ደ​ር​ገው ምንም የለም። መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመ​ብል ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሁለ​ቱ​ንም ይሽ​ራ​ቸ​ዋል፤ ሥጋ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ለዝ​ሙት አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሥ​ጋ​ችሁ ነው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ያስ​ነ​ሣው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኛ​ንም በከ​ሃ​ሊ​ነቱ ያስ​ነ​ሣ​ናል። ሥጋ​ችሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን አካል ወስ​ዳ​ችሁ የአ​መ​ን​ዝራ አካል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ች​ሁን? አይ​ገ​ባም። ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የተ​ዋ​ሐደ ግን ከእ​ርሱ ጋር አንድ መን​ፈስ ይሆ​ናል። ከዝ​ሙት ራቁ፤ ኀጢ​አት የሚ​ሠራ ሰው ሁሉ ከሥ​ጋው ውጭ ይሠ​ራ​ልና፤ ዝሙ​ትን የሚ​ሠራ ግን ራሱ በሥ​ጋው ላይ ኀጢ​አ​ትን ይሠ​ራል። ሥጋ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት በእ​ና​ንተ አድሮ ላለ ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? ለራ​ሳ​ች​ሁም አይ​ደ​ላ​ች​ሁም። በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።

1 ቆሮንቶስ 6:12-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ምንም ነገር በእኔ ላይ አይሠለጥንም። ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው። እግዚአብሔር ጌታን ከሙታን እንዳስነሣው፣ እኛንም ደግሞ በኀይሉ ከሙታን ያስነሣናል። ሰውነታችሁ የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? ታዲያ፣ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ ከዝሙት ዐዳሪ ብልቶች ጋራ አንድ ላድርገውን? ከቶ አይሆንም! ወይስ ከዝሙት ዐዳሪ ጋራ የሚተባበር ሰው ከርሷ ጋራ አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሏልና። ነገር ግን ከጌታ ጋራ የሚተባበር ከርሱ ጋራ አንድ መንፈስ ይሆናል። ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል። ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

1 ቆሮንቶስ 6:12-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤ እግዚአብሔርም ጌታንም አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል። ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም። ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና። ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

1 ቆሮንቶስ 6:12-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ግን ሁሉም ነገር ይጠቅመኛል ማለት አይደለም፤ ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል፤ ይሁን እንጂ ለማናቸውም ነገር ባሪያ ሆኜ አልገዛም፤ “ምግብ ለሆድ፥ ሆድም ለምግብ ነው፤” ታዲያ፥ እግዚአብሔር ምግብንም፥ ሆድንም ያጠፋቸዋል፤ ነገር ግን ሰውነታችን ለጌታ ኢየሱስ፥ ጌታ ኢየሱስም ለሰውነታችን ስለ ሆነ ሰውነታችንን ለዝሙት ማዋል አይገባንም። እግዚአብሔር ጌታ ኢየሱስን ከሞት አስነሥቶታል፤ እኛንም በኀይሉ ከሞት ያስነሣል። ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ክፍል መሆኑን ታውቁ የለምን? ታዲያ፥ የክርስቶስን አካል ክፍል ወስጄ የአመንዝራ ሴት አካል ክፍል እንዲሆን ላደርገው ይገባልን? ከቶ አይገባም! ከአመንዝራ ሴት ጋር የሚገናኝ ሰው ከእርስዋ ጋር አንድ አካል መሆኑን ታውቁ የለምን? “ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎ ተጽፎአልና። ከጌታ ኢየሱስ ጋር የሚተባበር ሰው ግን ከእርሱ ጋር በመንፈስ አንድ ይሆናል። ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤ ሰውነታችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን ታውቁ የለምን? እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም። እርሱ በዋጋ ገዝቶአችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

1 ቆሮንቶስ 6:12-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤” ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው፤ እግዚአብሔርም ጌታን ከሞት አስነሣ፥ እኛንም በኀይሉ ያስነሣናል። ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል እንደሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን የአካል ክፍሎች ወስጄ የአመንዝራ ክፍሎች አካል ላድርጋቸውን? ፈጽሞ ከቶ አይገባም። ወይስ ከአመንዝራ ጋር የሚገናኝ አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤” ተብሏልና። ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአትን ይሠራል። ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም። በዋጋ ተገዝታችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።