1 ቆሮንቶስ 2:1-4
1 ቆሮንቶስ 2:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም። ከተሰቀለው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በእናንተ ዘንድ ሌላ ነገር እሰማለሁ ብዬ አልጠረጠርሁም ነበር። እኔም በድካምና በፍርሀት፥ በብዙ መንቀጥቀጥም መጣሁ። ቃሌም፥ ትምህርቴም መንፈስንና ኀይልን በመግለጥ ነበር እንጂ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
1 ቆሮንቶስ 2:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና። ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሀት፣ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር። ቃሌም ስብከቴም የመንፈስን ኀይል በመግለጥ እንጂ፣ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤
1 ቆሮንቶስ 2:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
1 ቆሮንቶስ 2:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር የመሰከርኩት የንግግርን ችሎታና የፍልስፍናን ጥበብ በማሳየት አይደለም። ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር በተለይም በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞቱን በቀር ሌላ ምንም ነገር ላለማወቅ ወስኜ ነበር። ስለዚህ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ደካማ ሆኜ በፍርሃትና በብዙ መንቀጥቀጥ ላይ ነበርኩ። ንግግሬና ስብከቴ በሰብአዊ ጥበብና ንግግር በማሳመር ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል የተደገፈ ነበር።
1 ቆሮንቶስ 2:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ወንድሞች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ የእግዚአብሔርን ምስጢር በቃላት መራቀቅ ወይም ጥበብ ለእናንተ ለማወጅ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር፥ እርሱም እንደ ተሰቀለ፥ ሌላ ነገር ላለማወቅ ወስኜ ነበርና። እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤