1 ዜና መዋዕል 4:9 - Compare All Versions

1 ዜና መዋዕል 4:9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው።

1 ዜና መዋዕል 4:9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።

1 ዜና መዋዕል 4:9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን “ያቤጽ” ብላ ጠራችው።

1 ዜና መዋዕል 4:9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤

1 ዜና መዋዕል 4:9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው።