የማቴዎስ ወንጌል 27:32-37

የማቴዎስ ወንጌል 27:32-37 አማ54

ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት። ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም። ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥ በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች