የዮሐንስ ወንጌል 4:13-17
የዮሐንስ ወንጌል 4:13-17 አማ54
ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤ እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው። ኢየሱስም፦ ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት። ሴቲቱ መልሳ፦ ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስም፦ ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤

