ትንቢተ ኢሳይያስ 33:2-6

ትንቢተ ኢሳይያስ 33:2-6 አማ54

አቤቱ፥ ማረን፥ አንተን ተማምነናል፥ ጥዋት ጥዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን። ከፊጅት ድምፅ ወገኖች ሸሹ፥ በመነሳትህም አህዛብ ተበተኑ። አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፥ ኩብኩባም እንደሚዘልል ሰዎች ይዘልሉበታል። እግዚአብሔርም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፥ ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት። የዘመንህም ጸጥታ የመድኃኒት ብዛት፥ ጥበብና እውቀት ይሆናል፥ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።