መጽሐፈ ዕዝራ 8
8
ከዕዝራ ጋር የተመለሱ የየጎሣው አለቆች
1በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ናቸው። ትውልዳቸውም ይህ ነው፤ 2ከፊንሐስ ልጆች ጌርሶን፥ ከኢታምር ልጆች ዳንኤል፥ ከዳዊት ልጆች ሐጡስ፥ ከሴኬንያ ልጆች፥ 3ከፋሮስ ልጆቾ ዛካርያስ፥ ከእርሱም ጋር መቶ አምሳ ወንዶች በትውልድ ተቈጠሩ። 4ከፋሐት ሞዓብ ልጆች የዘራእያ ልጅ ኤሊሆዔናይ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ወንዶች። 5ከሴኬንያ ልጆች የየሕዚኤል ልጅ፥ ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ወንዶች። 6ከዓዲን ልጆች የዮናታን ልጅ ዔቤድ፥ ከእርሱም ጋር አምሳ ወንዶች። 7ከኤላም ልጆች የጎቶልያ ልጅ የሻያ፥ ከእርሱም ጋር ሰባ ወንዶች። 8ከሰፋጥያስ ልጆች የሚካኤል ልጅ ዝባድያ፥ ከእርሱም ጋር ሰማንያ ወንዶች። 9ከኢዮአብ ልጆች የይሒኤል ልጅ አብድዩ፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ አሥራ ስምንት ወንዶች። 10ከሰሎሚት ልጆች የዮሲፍያ ልጅ፥ ከእርሱም ጋር መቶ ስድሳ ወንዶች። 11ከቤባይ ልጆች የቤባይ ልጅ ዘካርያስ፥ ከእርሱም ጋር ሀያ ስምንት ወንዶች። 12ከዓዝጋድ ልጆች የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን፥ ከእርሱም ጋር መቶ አሥር ወንዶች። 13ከኋለኞቹ ከአዶኒቃም ልጆች ስማቸው ይህ ነው፤ ኤሊፋላት፥ ይዑኤል፥ ሸማያ፥ ከእነርሱም ጋር ስድሳ ወንዶች። 14ከበጉዋይ ልጆች ዑታይና ዘቡድ፥ ከእነርሱም ጋር ሰባ ወንዶች።
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች
15ወደ አኅዋም ወደሚፈስስ ወንዝ ሰበሰብኋቸው፤ በዚያም ሦስት ቀን ሰፈርን፤ ሕዝቡንና ካህናቱን ስቈጥራቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማንንም አላገኘሁም። 16ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሸማያ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ኤልናታን ላክሁ። 17በካሲፍያ ስፍራ ወደ ነበረው ወደ አለቃው ወደ አዶ ላክኋቸው፤ ለአምላካችን ቤት አገልጋዮችን ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለአዶና ለወንድሞቹ ለናታኒም የሚነግሩአቸውን በአፋቸው አደረግሁ። 18በላያችንም መልካም በሆነው በአምላካችን እጅ ከእስራኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞሖሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሰራብያን፥ ከእርሱም ጋር አሥራ ስምንቱን ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን። 19ደግሞም ሐሸብያን ከእርሱም ጋር ከሜራሪ ልጆች ወገን የነበረውን የሻያንና ሀያውን ወንድሞቹንና ልጆቻቸውን። 20ሌዋውያንንም እንዲያገለግሉ ዳዊትና አለቆቹ ከሰጡአቸው ናታኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሀያ ናታኒም አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በስም በስማቸው ተጠሩ።
ለጥበቃ ጾምና ጸሎት እንደተደረገ
21በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ። 22ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና። 23ስለዚህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።
ለቤተ መቅደሱ የቀረቡ ስጦታዎች
24ከካህናቱም አለቆች አሥራ ሁለት ሰዎችን፥ ሰራብያንና ሐሸቢያን ከእነርሱም ጋር አሥር ወንድሞቻቸውን ለየሁ፤ 25ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹና በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው። 26ስድስት መቶ አምሳ መክሊት ብር፥ አንድ መቶም መክሊት የብር ዕቃዎች፥ አንድ መቶም መክሊት ወርቅ፥ 27ሀያም ባለሺህ ዳሪክ የወርቅ ጽዋዎች፥ ሁለትም እንደ ወርቅ የከበሩ ከጥሩ ከሚያንጸባርቅ ናስ የተሠሩ ዕቃዎች መዝኜ በእጃቸው ሰጠሁ። 28እኔም፦ “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤ 29በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው። 30ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ።
ዕዝራና ሕዝቡ ኢየሩሳሌም እንደደረሱ
31በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፤ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን። 32ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን። 33በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርዮ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። 34ሁሉም በቍጥርና በሚዛን ተመዘነ፤ ሚዛኑም ሁሉ በዚያን ጊዜ ተጻፈ።
35ከምርኮም የወጡት ምርኮኞች ለእስራኤል አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶችና ለኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። 36የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዝ ማዶ ላሉት ለንጉሡ ሹማምቶችና ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዕዝራ 8: አማ54
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ