ትን​ቢተ ዘካ​ር​ያስ 4:8-10

ትን​ቢተ ዘካ​ር​ያስ 4:8-10 አማ2000

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።