መጽሐፈ ሲራክ 33
33
ስለ እስራኤል ድኅነት የቀረበ ጸሎት
1የኀይል ሁሉ ፈጣሪ አቤቱ፥ ይቅር በለን፤ ተመለስልንም።
2በአሕዛብ ሁሉ ላይ አንተን መፍራትን አሳድር።
3ልዩ በሆኑ ወገኖችም ላይ እጅህን አንሣ፤
ኀይልህንም ይዩ።
4እነርሱ እያዩ በእኛ ዘንድ እንደ ተመሰገንህ፥
እንደዚሁ እኛ እያየን በእነርሱ ዘንድ ተመስገን።
5አቤቱ ያለአንተ ሌላ ፈጣሪ የለምና፥
እኛ እንዳወቅንህ እነርሱም ይወቁህ።
6ተአምራትህን አሳይ፤
ጌትነትህንም ግለጥ።
7በእጅህ ኀይል በቀኝህም ክብር፥
8ጥፋትን አምጣባቸው፤
መቅሠፍትንም ላክባቸው።
9ዐመፀኛውንም አጥፋው፤
ጠላትንም ቀጥቅጠው።
10ድንቅ ሥራህን ይነግሩ ዘንድ የባሮችህን መሐላ አስብ፤
የሚጠፉባትንም ቀን ፈጥነህ አድርጋት።
11በቍጣና በእሳት ቅሠፋቸው፤
ከእነርሱም ያመለጡትን አጥፋቸው፤
በወገኖችህም ላይ ክፉ ያደረጉ ሰዎችን ሞት ያግኛቸው።
12ያለ እኛ ሌላ ሰው የለም የሚሉ የጠላቶችን አለቆች ራስ ስበር።
13የያዕቆብን ልጆች ሁሉ ሰብስባቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 33: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ