መጽ​ሐፈ ሲራክ 19

19
1ሰካ​ራም ሠራ​ተኛ አይ​በ​ለ​ጥ​ግም፥
ጥቂ​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ብዙ​ውን ያጠ​ፋል።
2መጠ​ጥና ሴት ጠቢ​ባ​ንን ያስ​ት​ዋ​ቸ​ዋል፥
ጋለ​ሞ​ታን የሚ​ከ​ተ​ላት በደ​ለኛ ነው።
3የዚ​ህም ፍጻ​ሜው ትልና ጥፋት ነው።
ደፋር ሰው​ነት ከመ​ከራ አት​ጠ​በ​ቅም።
4ፈጥኖ የሚ​ያ​ምን ልቡ​ናው ቀሊል ነው፥
ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠ​ራም ራሱን ይበ​ድ​ላል።
5ልቡ​ና​ውን ደስ የሚ​ያ​ሰኝ ሰው ይደ​ነ​ቃል።
6ብዙ መና​ገ​ር​ንም የሚ​ጠላ ኀጢ​አ​ቱን ያሳ​ን​ሣል።
7የሰ​ማ​ኸ​ውን ቃል አታ​ውጣ፥ አት​ድ​ገ​መ​ውም፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም የባሰ አያ​ገ​ኝ​ህም።
8በወ​ዳ​ጅና በጠ​ላት ዘንድ የም​ት​ና​ገ​ረው ነገር አይ​ኑር፥
ስተህ የሠ​ራ​ኸው ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አት​ና​ገር።
9ቢሰማ አይ​ሰ​ው​ር​ል​ህ​ምና፥
እስ​ክ​ት​ሞ​ትም ድረስ ይጠ​ብ​ቅ​ሃል።
10የሰ​ማ​ኸ​ውን ቃል አታ​ውጣ፥
ከዚ​ህም በኋላ የሚ​ያ​ገ​ኝህ ክፉ ነገር እን​ደ​ሌለ እመን።
11አላ​ዋቂ ሰው የሰ​ማ​ውን ነገር እስ​ከ​ሚ​ያ​ወጣ ድረስ ይቅ​በ​ዘ​በ​ዛል፥
ልጅ የም​ት​ወ​ልድ ሴትም በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነቅ ይጨ​ነ​ቃል።
12የተ​ወጋ ሰውም ጦሩን ከላዩ ይነ​ቅል ዘንድ እን​ደ​ሚ​ቸ​ኩል፥
አላ​ዋቂ ሰው የሰ​ማ​ውን ቃል ያወጣ ዘንድ ይቸ​ኩ​ላል።
13ወዳ​ጅ​ህን አላ​ደ​ረገ እንደ ሆነ
ወይም አድ​ርጎ እንደ ሆነ እን​ዳ​ይ​ደ​ግም ገሥ​ጸው።
14ወዳ​ጅ​ህን፥ አል​ተ​ና​ገረ እንደ ሆነ
ወይም ተና​ግሮ እንደ ሆነ እን​ዳ​ይ​ደ​ግም ገሥ​ጸው።
15ወዳ​ጅ​ህን በጥ​ላቻ ነገር ተሠ​ር​ቶ​በት ይሆ​ና​ልና ገሥ​ጸው፤
ከልቡ ሳይ​ፈ​ቅድ የሚ​ሳ​ሳት ሰው አለና የነ​ገ​ሩ​ህን ነገር ሁሉ አት​መን።
16በአ​ን​ደ​በቱ የማ​ይ​ሳ​ሳት ማን ነው?
17ቍጣ ሳይ​በዛ ወዳ​ጅ​ህን ገሥ​ጸው፥
ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግም ቍጣን አሳ​ል​ፋት።
18ጥበብ ሁላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ናትና፥
ጥበ​ብም ሁላ ሕጉን ታስ​ጠ​ብ​ቃ​ለ​ችና።
እው​ነ​ተ​ኛና ሐሰ​ተኛ ጥበብ
19ክፉን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር ጥበብ የለም፥
ለኃ​ጥ​ኣ​ንም ምክር ጥበብ የላ​ትም።
20ከሁሉ የም​ት​ረ​ክስ ክፋት አለች፥
አእ​ምሮ የጐ​ደ​ለው አላ​ዋ​ቂም አለ።
21ነገር ግን ከሚ​ራ​ቀቅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ ከሚ​ክድ ይልቅ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ አላ​ዋቂ ይሻ​ላል።
22እየ​በ​ደለ የሚ​ራ​ቀ​ቅና የሚ​ጠ​ነ​ቀቅ አለ፥
ለባ​ል​ን​ጀ​ራው የሚ​ያ​ደላ፥ ለወ​ዳ​ጁም ፍር​ድን የሚ​ያ​ቀና መስሎ ፍር​ድን የሚ​ለ​ውጥ ሰው አለ።
23እያ​መ​ሰ​ገነ ለክፉ ነገር የሚ​ያ​ደላ ሰው አለ፥
ልቡ​ናው ግን ሽን​ገ​ላን ተሞ​ል​ት​ዋል።
24በል​ቡ​ናው ሌላ ነገር እያለ ፊት አይቶ የሚ​ያ​ዳላ አለ፥
ባላ​ሰ​ብ​ኸ​ውም ነገር ይመ​ጣ​ብ​ሃል።
25ኀይሉ ቢደ​ክም፥ በአ​ን​ተም ላይ ክፉ ማድ​ረግ ቢሳ​ነው፥
ያስ​ትህ ዘንድ መከ​ራን በግድ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።
26ሰው በመ​ልኩ ይታ​ወ​ቃ​ልና፥ ጠቢ​ብም በገጹ ይታ​ወ​ቃል።
27ካለ​ባ​በ​ሱና ካካ​ሄዱ፥ ከአ​ሳ​ሣ​ቁም የተ​ነሣ፥
የሰው ጠባዩ ይታ​ወ​ቃል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ