የኦሪት ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለን፤ እኔ ግን ለኀጢአት የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ። የማደርገውን አላውቅምና፤ የምወደውንም ያን ምንም አላደርገውምና፤ ያንኑ የምጠላውን ብቻ እሠራለሁ እንጂ። የማልወደውን የምሠራ ከሆንሁ ግን ያ የኦሪት ሕግ መሠራት ለበጎ እንደ ሆነ ምስክሩ እኔ ነኝ። እንግዲያስ በእኔ ላይ ያደረች ኀጢአት ናት እንጂ፥ ያን የማደርገው እኔ አይደለሁም። በእኔ ማለት በሥጋዬ መልካም ነገር እንደማይኖር አውቃለሁ፤ መልካም ሥራ ለመሥራት መሻቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግባር መሥራት ግን የለኝም። ያን የምወደውንም በጎ ነገር የማደርግ አይደለም፤ ነገር ግን ያን የምጠላውን ክፉውን አደርጋለሁ። የማልወደውንስ የምሠራ ከሆነ የምሠራው እኔ አይደለሁም፤ በእኔ ላይ ያደረች ኀጢአት ናት እንጂ። መልካም ሥራ እንድሠራ የፈቀደልኝን ያን ሕግ እርሱ ክፉ ነገር አምጥቶብኝ አገኘሁት። በልቡናዬ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር ሕግ መልካም ነው። ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ፤ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ፤ በሰውነቴ ውስጥ ያለው ያ የኀጢአት ሕግም በረታና ወደ እርሱ ማረከኝ። እኔ ምንና ወራዳ ሰው ነኝ፤ ከዚህ ሟች ሰውነቴ ማን ባዳነኝ?
ወደ ሮሜ ሰዎች 7 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 7
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 7:14-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች