ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6-15

ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6-15 አማ2000

ክር​ስ​ቶ​ስም እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ይሞት ዘንድ ዘመኑ ሲደ​ርስ መጣ። ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን ያህል እንደ ወደ​ደን እነሆ፥ እዩ፤ እና ኀጢ​አ​ተ​ኞች ስን​ሆን ክር​ስ​ቶስ ስለ እና ሞተ። እን​ግ​ዲህ በደሙ ዛሬ ከጸ​ደ​ቅን ከሚ​መ​ጣው መከራ በእ​ርሱ እን​ድ​ና​ለን። እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶቹ ስን​ሆን በልጁ ሞት ይቅር ካለን፥ ከታ​ረ​ቀን በኋ​ላም በልጁ ሕይ​ወት እን​ዴት የበ​ለጠ ያድ​ነን! በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ። ስለ​ዚ​ህም በአ​ንድ ሰው በደል ምክ​ን​ያት ኀጢ​አት ወደ ዓለም ገባች፤ ስለ​ዚ​ችም ኀጢ​አት ሞት ገባ፤ እን​ደ​ዚ​ሁም ሁሉ ኀጢ​አ​ትን ስለ አደ​ረጉ በሰው ሁሉ ላይ ሞት መጣ። ኦሪት እስከ መጣች ድረስ ኀጢ​አት ምን እንደ ሆነች ሳት​ታ​ወቅ በዓ​ለም ውስጥ ነበ​ረች፤ ነገር ግን የኦ​ሪት ሕግ ገና ስላ​ል​መጣ ኀጢ​አት ተብላ አት​ቈ​ጠ​ርም ነበር። ነገር ግን በአ​ዳም ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ከአ​ዳም እስከ ሙሴ የበ​ደ​ሉ​ት​ንም ያል​በ​ደ​ሉ​ት​ንም ሞት ገዛ​ቸው፤ ሁሉ በአ​ዳም አም​ሳል ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፥ አዳ​ምም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእ​ርሱ አም​ሳሉ ነውና። ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በበ​ደ​ላ​ችን መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ በአ​ንድ ሰው በደል ብዙ​ዎች ከሞቱ፥ እን​ግ​ዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ፥ በአ​ንዱ ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቤዛ​ነት በሰ​ጠን ሀብቱ ሕይ​ወት በብ​ዙ​ዎች ላይ እን​ዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}