ወደ ሮሜ ሰዎች 3:21-30

ወደ ሮሜ ሰዎች 3:21-30 አማ2000

አሁን ግን በኦ​ሪ​ትና በነ​ቢ​ያት የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገ​ለ​ጠች። የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይጸ​ድ​ቃሉ። በዚ​ህም ልዩ​ነት የለም፤ ሁሉም ፈጽ​መው በድ​ለ​ዋ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማክ​በ​ር​ንም ትተ​ዋ​ልና። ጽድቅ ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ቤዛ​ነት ያለ ዋጋ በእ​ርሱ ቸር​ነት ሆነ። እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጋሽ በመ​ሆኑ፥ እሺ በማ​ለ​ቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም የሚ​ያ​ም​ኑ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​ጸ​ድ​ቃ​ቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው። ትም​ክ​ሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀር​ቶ​አል፤ በየ​ት​ና​ውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ሕግ ነው እንጂ። ሰው የኦ​ሪ​ትን ሥራ ሳይ​ሠራ በእ​ም​ነት እን​ዲ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና። በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ይ​ሁድ ለብ​ቻ​ቸው ነውን? ለአ​ሕ​ዛ​ብስ አይ​ደ​ለ​ምን? አዎን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነው፤ የተ​ገ​ዘ​ረ​ውን በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረ​ው​ንም በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው እርሱ አንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።