ወደ ሮሜ ሰዎች 2:21-22

ወደ ሮሜ ሰዎች 2:21-22 አማ2000

እን​ግ​ዲህ ሌላ​ውን የም​ታ​ስ​ተ​ምር ራስ​ህን እን​ዴት አታ​ስ​ተ​ም​ርም? አት​ስ​ረቁ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ትሰ​ር​ቃ​ለህ። አታ​መ​ን​ዝሩ ትላ​ለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመ​ነ​ዝ​ራ​ለህ፤ ወደ ጐል​ማሳ ሚስ​ትም ትሄ​ዳ​ለህ፤ ጣዖ​ትን ትጸ​የ​ፋ​ለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅ​ደ​ስን ትዘ​ር​ፋ​ለህ።