ወደ ሮሜ ሰዎች 10:1-4

ወደ ሮሜ ሰዎች 10:1-4 አማ2000

ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲ​ቀኑ ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና፤ ነገር ግን ዐው​ቀው አይ​ደ​ለም። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ አያ​ው​ቁ​አ​ት​ምና በራ​ሳ​ቸ​ውም ጽድቅ ጸን​ተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ግን መገ​ዛት ተሳ​ና​ቸው። የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።