የዮ​ሐ​ንስ ራእይ 22:1-3

የዮ​ሐ​ንስ ራእይ 22:1-3 አማ2000

በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ። በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ። ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፤ ፊቱንም ያያሉ፤