“አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥ ከዐመፀኛ ሰውም ታደገኝ፥ ሁልጊዜ በልባቸው ዐመፃን የሚመክሩ፥ ይገድሉኝ ዘንድ ይከብቡኛል። ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፤ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ። አቤቱ፥ ከኃጥኣን እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዐመፀኞች ሰዎች አድነኝ። ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥ ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፤ በመንገዴም ዕንቅፋትን አኖሩ። እግዚአብሔርንም፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ” አልሁት። አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የድኅነቴ ኀይል፥ በጦርነት ቀን በራሴ ላይ ሁነህ ሰወርኸኝ።
መዝሙረ ዳዊት 139 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 139:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች