መዝ​ሙረ ዳዊት 112:1-9

መዝ​ሙረ ዳዊት 112:1-9 አማ2000

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ዎች ሆይ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም አመ​ስ​ግኑ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ቡሩክ ይሁን። ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያው ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይመ​ስ​ገን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥ ክብ​ሩም ከሰ​ማ​ያት በላይ ነው። እንደ አም​ላ​ካ​ችን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? በል​ዕ​ልና የሚ​ኖር። በሰ​ማ​ይና በም​ድር የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን የሚ​ያይ፤ ድሃ​ውን ከም​ድር የሚ​ያ​ነሣ፥ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከመ​ሬት ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ፤ ከአ​ለ​ቆች ጋር ከሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች ጋር ያኖ​ረው ዘንድ መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።