ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:14-16
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:14-16 አማ2000
ነገር ግን በመከራዬ ጊዜ ተባባሪዎች መሆናችሁ መልካም አደረጋችሁ። እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች፤ በመጀመሪያው ትምህርት ከመቄዶንያ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመስጠትም ቢሆን፥ በመቀበል ከእኔ ጋር እንዳልተባበሩ እናንተ ታውቃላችሁ። በተሰሎንቄም ሳለሁ ደግሞ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ለችግሬ ላካችሁልኝ።