ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 3:4-11

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 3:4-11 አማ2000

እኔም ግዝ​ረት ሳለኝ በግ​ዝ​ረት አል​መ​ካም፤ በግ​ዝ​ረት መመ​ካ​ትን የሚ​ያ​ስብ ካለም እኔ እር​ሱን እበ​ል​ጠ​ዋ​ለሁ። በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የተ​ገ​ዘ​ርሁ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከብ​ን​ያም ነገድ ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ዕብ​ራዊ ነኝ፤ በኦ​ሪ​ትም ፈሪ​ሳዊ ነበ​ርሁ። በኦ​ሪት ጽድ​ቅም ያለ ነውር ሆኜ በቅ​ን​ዐት ምእ​መ​ና​ንን አሳ​ድድ ነበር። ነገር ግን ስለ ክር​ስ​ቶስ ያን ጥቅ​ሜን ላጣው ወደ​ድሁ። ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት። በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ። በእ​ር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ነ​ሣ​ቱ​ንም ኀይል በሕ​ማሙ እሳ​ተ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ በሞ​ቱም እመ​ስ​ለ​ዋ​ለሁ። ይኸ​ውም ሙታን በሚ​ነሡ ጊዜ ምና​ል​ባት በዚህ አገ​ኘው እንደ ሆነ ብዬ ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}