የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 3:1-5

የማ​ር​ቆስ ወን​ጌል 3:1-5 አማ2000

ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤ ሊከሱትም በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር። እጁ የሰለለችውንም ሰው “ተነሥተህ ወደ መካከል ና፤” አለው። “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል?” አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ። ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፤ ሰውየውንም “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እጁም ዳነች።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች