የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 15:13-21

የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 15:13-21 አማ2000

እርሱ ግን መልሶ “የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ። ጴጥሮስም መልሶ “ምሳሌውን ተርጕምልን፤” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለ “እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።” ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች