የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6:17-19

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 6:17-19 አማ2000

ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመ​ላው ይሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ከጢ​ሮ​ስና ከሲ​ዶና ባሕር ዳርቻ ትም​ህ​ር​ቱን ሊሰሙ፥ ከደ​ዌ​አ​ቸ​ውም ሊፈ​ወሱ የመ​ጡት ከሕ​ዝቡ ወገን እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ። ክፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ይፈ​ወሱ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ ሊዳ​ስ​ሱት ይሹ ነበር፤ ኀይል ከእ​ርሱ ይወጣ ነበ​ርና፥ ሁሉ​ንም ይፈ​ው​ሳ​ቸው ነበር።