የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24:13-25

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 24:13-25 አማ2000

በዚ​ያም ቀን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስድሳ ምዕ​ራፍ ያህል ወደ​ም​ት​ር​ቀው ኤማ​ሁስ ወደ​ም​ት​ባ​ለው መን​ደር ሄዱ። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ር​ሱም ይህን ሲነ​ጋ​ገ​ሩና ሲመ​ራ​መሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ እነ​ርሱ ቀረበ፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ሄደ። እን​ዳ​ያ​ው​ቁ​ትም ዐይ​ና​ቸው ተይዞ ነበር። ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም ቀለ​ዮጳ የሚ​ባ​ለው አንዱ መልሶ፥ “አንተ ብቻ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ግዳ ነህን? በእ​ነ​ዚህ ቀኖ​ችስ በው​ስ​ጥዋ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህ ምን​ድ​ነው?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በቃ​ሉና በሥ​ራው ብርቱ ነቢ​ይና እው​ነ​ተኛ ሰው ስለ​ነ​በ​ረው ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና መኳ​ን​ን​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ል​ፈው እንደ ሰጡት፥ ሞትም እንደ ፈረ​ዱ​በ​ትና እንደ ሰቀ​ሉት ነው። እኛ ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ እና​ደ​ርግ ነበር፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ይህ ነገር ከሆነ ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀን ነው። ደግ​ሞም ሴቶች ከእኛ ዘንድ ወደ መቃ​ብር ገስ​ግ​ሠው ሄደው ነበ​ርና አስ​ደ​ን​ቀው ነገ​ሩን። ሥጋ​ው​ንም በአ​ላ​ገኙ ጊዜ ተመ​ል​ሰው፦ ተነ​ሥ​ቶ​አል ያሉ​አ​ቸ​ውን የመ​ላ​እ​ክ​ትን መልክ እንደ አዩ ነገ​ሩን። ከእ​ኛም ዘንድ ወደ መቃ​ብር ሄደው እን​ዲሁ ሴቶች እንደ ተና​ገ​ሩት ሆኖ ያገ​ኙት አሉ፤ እር​ሱን ግን አላ​ዩ​ትም።” ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰነ​ፎች፥ ነቢ​ያ​ትም የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ነገር ሁሉ ከማ​መን ልባ​ችሁ የዘ​ገየ፥