የሉ​ቃስ ወን​ጌል 20:9-18

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 20:9-18 አማ2000

ለሕ​ዝ​ቡም ይህን ምሳሌ ይመ​ስ​ል​ላ​ቸው ጀመረ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭ​መ​ቂ​ያም አስ​ቈ​ፈረ፤ ግን​ብም ሠራ​ለት፤ ለገ​ባ​ሮ​ችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይ​መ​ለ​ስም ዘገየ። የመ​ከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባ​ሮቹ፥ ከወ​ይኑ ፍሬ ይል​ኩ​ለት ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ ገባ​ሮቹ ግን አገ​ል​ጋ​ዩን ደብ​ድ​በው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት። ዳግ​መ​ኛም ሌላ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም ደብ​ድ​በ​ውና አዋ​ር​ደው ባዶ እጁን ሰደ​ዱት። ደግሞ ሦስ​ተ​ኛ​ውን አገ​ል​ጋ​ዩን ላከ፤ እር​ሱ​ንም አቍ​ስ​ለው ሰደ​ዱት። የወ​ይኑ ባለ​ቤ​ትም፦ እን​ግ​ዲህ ምን ላድ​ርግ? ምና​ል​ባት እር​ሱን እንኳ አይ​ተው ያፍሩ እንደ ሆነ የም​ወ​ደ​ውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው። ገባ​ሮ​ቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና ርስ​ቱን እን​ው​ሰድ ብለው ተማ​ከሩ። ከወ​ይኑ ቦታም ወደ ውጭ አው​ጥ​ተው ገደ​ሉት። የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ተመ​ለ​ከ​ተና እን​ዲህ አላ​ቸው፤ “ግን​በ​ኞች የና​ቁ​አት ድን​ጋይ እር​ስዋ የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነች፥ የሚ​ለው ጽሑፍ ምን​ድ​ነው? በዚ​ያች ድን​ጋይ ላይ የወ​ደቀ ሁሉ ይቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ እር​ስ​ዋም የወ​ደ​ቀ​ች​በ​ትን ታደ​ቅ​ቀ​ዋ​ለች።”