ለሕዝቡም ይህን ምሳሌ ይመስልላቸው ጀመረ፤ እንዲህም አላቸው፥ “አንድ ሰው ወይን ተከለ፤ መጭመቂያም አስቈፈረ፤ ግንብም ሠራለት፤ ለገባሮችም ሰጥቶ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ፤ ሳይመለስም ዘገየ። የመከሩ ወራት በሆነ ጊዜም ወደ ገባሮቹ፥ ከወይኑ ፍሬ ይልኩለት ዘንድ አገልጋዩን ላከ፤ ገባሮቹ ግን አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን ሰደዱት። ዳግመኛም ሌላውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን ሰደዱት። ደግሞ ሦስተኛውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም አቍስለው ሰደዱት። የወይኑ ባለቤትም፦ እንግዲህ ምን ላድርግ? ምናልባት እርሱን እንኳ አይተው ያፍሩ እንደ ሆነ የምወደውን ልጄን ልላክ ብሎ ላከው። ገባሮቹም ባዩት ጊዜ ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፥ እንግደለውና ርስቱን እንውሰድ ብለው ተማከሩ። ከወይኑ ቦታም ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት። የወይኑ ባለቤት በመጣ ጊዜ እንግዲህ ምን ያደርጋቸዋል? ይመጣል፤ እነዚያንም ገባሮች ይገድላቸዋል፤ ወይኑንም ለሌሎች ገባሮች ይሰጣል፤” ቃሉንም ሰምተው፥ “አይሆንም፤ እንዲህ አይደረግም” አሉ። ጌታችን ኢየሱስም ተመለከተና እንዲህ አላቸው፤ “ግንበኞች የናቁአት ድንጋይ እርስዋ የማዕዘን ራስ ሆነች፥ የሚለው ጽሑፍ ምንድነው? በዚያች ድንጋይ ላይ የወደቀ ሁሉ ይቀጠቀጣል፤ እርስዋም የወደቀችበትን ታደቅቀዋለች።”
የሉቃስ ወንጌል 20 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 20
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 20:9-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች