የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2:14-20

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2:14-20 አማ2000

“ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማ​ያት፥ ሰላ​ምም በም​ድር፥ ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” ይሉ ነበር። ከዚ​ህም በኋላ መላ​እ​ክት ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በዐ​ረጉ ጊዜ እነ​ዚያ እረ​ኞች ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “እስከ ቤተ ልሔም እን​ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የገ​ለ​ጠ​ል​ንን ይህን ነገር እን​ወቅ” አሉ። ፈጥ​ነ​ውም ሄዱ፤ ማር​ያ​ም​ንና ዮሴ​ፍን አገ​ኙ​አ​ቸው፤ ሕፃ​ኑ​ንም በበ​ረት ውስጥ ተኝቶ አገ​ኙት። በአ​ዩም ጊዜ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ስለ​ዚህ ሕፃን እንደ ሆነ ዐው​ቀው አወሩ። የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እረ​ኞቹ የነ​ገ​ሩ​አ​ቸ​ውን አደ​ነቁ። ማር​ያም ግን ይህን ሁሉ ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር። እረ​ኞ​ችም እንደ ነገ​ሩ​አ​ቸው ባዩ​ትና በሰ​ሙት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በ​ሩና እያ​መ​ሰ​ገኑ ተመ​ለሱ።

ከ የሉ​ቃስ ወን​ጌል 2:14-20ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች