ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር። እነሆ፥ የቀራጮች አለቃ ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ባለጸጋ ነበር። ጌታችን ኢየሱስንም ያየው ዘንድ፥ ማን እንደ ሆነም ያውቅ ዘንድ ይሻ ነበር፤ የሰው ብዛትም ይከለክለው ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበርና። ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘንድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚያች መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና። ጌታችን ኢየሱስም ወደዚያ በደረሰ ጊዜ አሻቅቦ አየውና፥ “ዘኬዎስ ሆይ፥ ፈጥነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ አለኝና” አለው። ፈጥኖም ወረደ፤ ደስ እያለውም ወደ ቤቱ ይዞት ገባ። ሁሉም አይተው “ወደ ኀጢኣተኛ ሰው ቤት ሊውል ገባ” ብለው አንጐራጐሩ። ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።” ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “ዛሬ ለዚህ ቤት ሕይወት ሆነ፤ እርሱ የአብርሃም ልጅ ነውና። የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና።” ይህንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገራቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦ ነበርና፤ እነርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት ወዲያውኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበርና። እንዲህም አለ፥ “አንድ የከበረ ሰው መንግሥት ይዞ ሊመለስ ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ። ዐሥሩን አገልጋዮቹንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና፦ እንግዲህ እስክመለስ ድረስ ነግዱ አላቸው። የሀገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነግሥ አንሻም ብለው አከታትለው መልእክተኞችን ላኩ። ከዚህም በኋላ፤ መንግሥትን ይዞ በተመለሰ ጊዜ እንደ አተረፉ ያውቅ ዘንድ ምናን የሰጣቸውን ብላቴኖቹን እንዲያመጡአቸው አዘዘ። አንደኛውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምናንህ ዐሥር ነበር፤ እነሆ ዐሥር ምናን አትርፌአለሁ አለው። ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለሆንህ በብዙ ላይ እሾምሃለሁ፤ በዐሥሩ ከተሞች ላይ ተሾም አለው። ሁለተኛውም መጥቶ፦ አቤቱ፥ ምናንህ አምስት ነበር፤ አምስት አትርፌአለሁ አለው። እርሱንም፦ አንተም በአምስት ከተሞች ተሾም አለው። ሦስተኛውም መጥቶ እንዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነበረቺው ምናንህ እነኋት፤ በጨርቅ ጠቅልዬ አኑሬአት ነበር። አንተ ያላኖርኸውን የምትወስድ፥ ያልዘራኸውን የምታጭድ፥ ያልበተንኸውንም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ ስለማውቅህ ፈርቼሃለሁና። ጌታውም እንዲህ አለው፦ አንተ ክፉ ሰነፍ አገልጋይ፥ እኔ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፥ ያልዘራሁትን የማጭድ፥ ያልበተንሁትንም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? እንደ ቃልህ እፈርድብሃለሁ። ለምን ገንዘቤን ወደ ለዋጮች አላስገባህም? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር በወሰድሁት ነበር። ከዚያ የቆሙትንም፦ ይህን ምናን ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር ምናን ላለው ስጡት አላቸው። እነርሱም አቤቱ፥ ዐሥር ምናን ያለው አይደለምን? አሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ላለው ሁሉ ይሰጡታል፤ ይጨምሩለታልም፤ የሌለውን ግን ያን ያለውንም ቢሆን ይወስዱበታል። ነገር ግን እነዚያን ልነግሥባቸው ያልወደዱትን ጠላቶችን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ውጉአቸው።” ይህንም ተናግሮ ወደ ፊት ሄደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ወጣ።
የሉቃስ ወንጌል 19 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 19
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 19:1-28
6 ቀናት
ገንዘብ እና ሃብት እንዴት ነው ከመንግስቱ ጋር የሚዛመዱት?
7 ቀናት
በኢየሱስ ፀጋ እንዴት ነው እየተለወጥኩ ያለሁት?
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች