የሉ​ቃስ ወን​ጌል 15:20-32

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 15:20-32 አማ2000

ተነ​ሥ​ቶም ወደ አባቱ ሄደ፤ አባ​ቱም ከሩቅ አየ​ውና ራራ​ለት፤ ሮጦም አን​ገ​ቱን አቅፎ ሳመው። ልጁም፦ ‘አባቴ ሆይ፥ በሰ​ማ​ይም፥ በፊ​ት​ህም በደ​ልሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ልጅህ ልባል አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ አንዱ አድ​ር​ገኝ’ አለው። አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’ የሰ​ባ​ውን ፍሪ​ዳም አም​ጡና እረዱ፤ እን​ብላ፤ ደስም ይበ​ለን። ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ነበር፤ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና ደስ ይላ​ቸ​ውም ጀመር። “ታላቁ ልጁም በእ​ርሻ ነበ​ርና ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ አጠ​ገብ በደ​ረሰ ጊዜ የዘ​ፈ​ኑ​ንና የመ​ሰ​ን​ቆ​ውን ድምፅ ሰማ። ከአ​ባቱ ብላ​ቴ​ኖ​ችም አን​ዱን ጠርቶ፦ ‘ይህ የም​ሰ​ማው ምን​ድን ነው?’ አለው። እር​ሱም፦ ‘ወን​ድ​ምህ ከሄ​ደ​በት መጣ፤ አባ​ት​ህም የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረደ፤ በሕ​ይ​ወት አግ​ኝ​ቶ​ታ​ልና’ አለው። ተቈ​ጥ​ቶም ‘አል​ገ​ባም’ አለ፤ አባ​ቱም ወጥቶ ማለ​ደው። መል​ሶም አባ​ቱን እን​ዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ፈጽሞ ከት​እ​ዛ​ዝህ አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ለእኔ ግን ከባ​ል​ን​ጀ​ሮች ጋር ደስ እን​ዲ​ለኝ አንድ የፍ​የል ጠቦት እንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም። ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’ አባ​ቱም እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ አን​ተማ እኮ ዘወ​ትር ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው። ነገር ግን ይህ ወን​ድ​ምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤ​ትም ልና​ደ​ርግ ይገ​ባል።”