ኦሪት ዘሌዋውያን 22
22
የመሥዋዕት ቅድስና
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ፥ የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 3እንዲህ በላቸው፦ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ በትውልዳችሁ ርኵሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 4ከአሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ሁሉ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሰው አይብላ። ከበድንም የተነሣ ርኩስ የሆነውን፥ ወይም ዘሩ ከእርሱ የሚፈስስበትን የሚነካ፥ 5ወይም የሚያረክሰውን ተንቀሳቃሽ፥ ወይም በሁሉ ዐይነት የረከሰውን ሰው የሚነካ፥ 6እነዚህን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ። 7ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ምግቡ ነውና ከተቀደሰው ይብላ። 8በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን፥ አውሬም የሰበረውን አይብላ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። 9ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ፥ ስለ እርስዋም ኀጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
10“ከባዕድ ወገን የሆነ ሰው ከተቀደሰው አይብላ፤ የካህኑም እንግዳ፥ ደመወዘኛውም ከተቀደሰው አይብላ። 11ካህኑ ግን በገንዘቡ አገልጋይ ቢገዛ እርሱ ከምግቡ ይብላ፤ በቤቱም የተወለዱት ከእንጀራው ይብሉ። 12የካህንም ልጅ ከሌላ ወገን ጋር ብትጋባ፥ እርስዋ ከተቀደሰው ዐሥራት አትብላ። 13የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነቷ እንደ ነበረች ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ፥ ከአባቷ እንጀራ ትብላ፤ ከሌላ ወገን የሆነ ባዕድ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ። 14ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ቢበላ አምስተኛ እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ለካህኑ ይስጥ። 15ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡትን፥ በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ። 16በኀጢአት ሳሉ ከተቀደሰው መሥዋዕት ከበሉ ግን ኀጢአትና በደል ይሆንባቸዋል፤ የማነጻቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
17እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 18“ለአሮንና ለልጆቹ፥ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ቤት ወይም ከእናንተ መካከል ከሚቀመጡት እንግዶች ማናቸውም ሰው ስእለቱን ሁሉ፥ በፈቃዱም የሚያቀርበውን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበውን ቍርባን ቢያቀርብ፥ 19ይሠምርላችሁ ዘንድ ከበሬ፥ ወይም ከበግ፥ ወይም ከፍየል ነውር የሌለበትን ተባቱን አቅርቡ። 20ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ነውር ያለበትን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ። 21ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በበዓላት ቀን” ይላል። የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሰምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነውርም አይሁንበት። 22ዕውር፥ ወይም ሰባራ፥ ወይም ምላሱ የተቈረጠ፥ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበት፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ እነዚህንም ለእሳት ቍርባን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአሔር አታሳርጉ። 23በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተቈረጠ ቢሆን፥ ቈጥረህ የራስህ ገንዘብ አድርገው እንጂ ለስእለት አይቀበልህም። 24የተቀጠቀጠውን፥ ወይም የተሰበረውን፥ ወይም የተቈረጠውን ወይም የተሰነጋውን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ፤ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ። 25ከእነዚህም ከባዕድ ወገን ከሆነ ሰው እጅ ለአምላካችሁ መባ አታቅርቡ፤ ርኵሰትም፥ ነውርም አለባቸውና አይቀበላችሁም።”
26እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 27“ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወለድ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን፥ ከዚያም በላይ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን የሠመረ ይሆናል። 28ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ። 29የምስጋናንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሠዉ እንዲቀበላችሁ ሠዉለት። 30በዚያው ቀን ይብሉት፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አትተዉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። 31ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ አድርጉትም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። 32የተቀደሰውንም ስሜን አታርክሱ፤ እኔ ግን በእስራኤል ልጆች መካከል እቀደሳለሁ፤ 33የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። አምላካችሁም እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 22: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ