መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7:1-3

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 7:1-3 አማ2000

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን እርም በሆ​ነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይ​ሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እር​ሱም የከ​ርሚ ልጅ፥ የዘ​ን​በሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆ​ነው ነገር ወሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ተቈጣ። ኢያ​ሱም ከቤ​ቴል በም​ሥ​ራቅ በኩል በቤ​ት​አ​ዊን አጠ​ገብ ወዳ​ለ​ችው ወደ ጋይ ሰዎ​ችን ከኢ​ያ​ሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይ​ንም ሰልሉ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹም ወጡ፤ ጋይ​ንም ሰለሉ። ወደ ኢያ​ሱም ተመ​ል​ሰው፥ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥ​ተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይ​ውጣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ሁሉ ግን ወደ​ዚያ አት​ው​ሰድ፤ ጥቂ​ቶች ናቸ​ውና” አሉት።