መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:12-14

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:12-14 አማ2000

ኢያ​ሱም በማ​ግ​ሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን ታቦት ተሸ​ከሙ። ሰባ​ቱም ካህ​ናት ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለ​ከ​ቱ​ንም ይነፉ ነበር፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም በፊ​ታ​ቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይነፉ ነበር። በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን የቀ​ረው ሕዝብ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ፤ ስድ​ስት ቀንም እን​ዲህ አደ​ረጉ።