መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:12-14
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6:12-14 አማ2000
ኢያሱም በማግሥቱ ማለዳ ተነሣ፤ ካህናቱም የእግዚአብሔርን የሕጉን ታቦት ተሸከሙ። ሰባቱም ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር፤ ተዋጊዎችም በፊታቸው ይሄዱ ነበር፤ የቀሩትም ሕዝብ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በኋላ ይሄዱ ነበር፤ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይነፉ ነበር። በሁለተኛውም ቀን የቀረው ሕዝብ ሁሉ ከተማዪቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲህ አደረጉ።

