መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 13:1-7

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 13:1-7 አማ2000

ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤ የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥ በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤ ከደ​ቡብ ጀምሮ በጋ​ዛና በሲ​ዶና ፊት ያለ​ውን የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ያለው የጌ​ባ​ላ​ው​ያን ምድር ሁሉ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች ካለ​ችው ጌል​ገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ያለ​ችው ሊባ​ኖስ ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከሊ​ባ​ኖስ ጀምሮ እስከ ማሴ​ሬ​ት​ሜ​ም​ፎ​ማ​ይም መያ​ያዣ ድረስ ሲዶ​ና​ው​ያን ሁሉ፤ እነ​ዚ​ህን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁ​ህም ምድ​ራ​ቸ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ር​ገህ አካ​ፍ​ላ​ቸው። አሁ​ንም ይህን ምድር ለዘ​ጠኙ ነገድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገህ ክፈ​ለው። ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በም​ዕ​ራብ እስ​ካ​ለው ታላቁ ባሕር ድረስ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል።”