መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1:1-11

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1:1-11 አማ2000

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “አገ​ል​ጋዬ ሙሴ ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም አን​ተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ​ም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ። ለሙሴ እንደ ነገ​ር​ሁት የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የሚ​ረ​ግ​ጠ​ውን ቦታ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ። ከሊ​ባ​ኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግ​ቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰ​ና​ችሁ ይሆ​ናል። በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ። አገ​ል​ጋዬ ሙሴ እንደ አዘ​ዘህ ሕግን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ጽና፤ እጅ​ግም በርታ፤ ሁሉን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሠራ ታውቅ ዘንድ ከእ​ርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አት​በል። የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ። እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።” ኢያ​ሱም የሕ​ዝ​ቡን ጻፎች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦ “በሰ​ፈሩ መካ​ከል ዕለፉ፥ ሕዝ​ቡ​ንም፦ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር እስከ ሦስት ቀን ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ልት​ወ​ር​ሱ​አት ትገ​ቡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁና ስን​ቃ​ች​ሁን አዘ​ጋጁ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}